ፕሬዚዳንት ትራምፕ ያደረጉትን ንግግር “ፍጹም ሃላፊነት የጎደለውና ዘመኑን የማይመጥን ነው”–የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ያደረጉትን ንግግር “ፍጹም ሃላፊነት የጎደለውና ዘመኑን የማይመጥን ነው”–የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያደረጉትን ንግግር “ፍጹም ሃላፊነት የጎደለው፣ ዘመኑን የማይመጥንና ከሚመሯት አገር የዴሞክራሲ ልምድና ትግበራ ጋር አብሮ የማይሄድ ነው” ሲል በጥብቅ አወገዘው።
ንግግሩ ግጭት ቀስቃሽና ቀጣናውን የሚያውክ መሆኑን ጉባኤው ለኢዜአ በላከው መግለጫ ገልጿል።
ፕሬዚዳንቱ ከሱዳንና የእስራኤል መሪዎች ጋር በነበራቸው የስልክ ውይይት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን አስመልክቶ የሰጡት አወዛጋቢ አስተያየት የአንድን አገር ሉአላዊነት ካለማክበርም አልፎ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ሃብት እየገነቡትን ያለውን የህዝብ ፕሮጀክት ለማስተጓጎል ታስቦ የተሰነዘረ በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሊያወግዘው እንደሚገባ አስገንዝቧል።
ኢትዮጵያ ግድቡን ለመገንባት ስትነሳ በአባይ ወንዝ መጠቀም ተፈጥሯዊ መብቷ ስለሆነና ውሃውን በፍትሃዊነት ለመጠቀም የሚያስችል አሰራር በመከተል እንደሆነ ያስታወሰው ጉባኤው፤ ይህ እየታወቀ በአድሎና ኢፍትሃዊ በሆነ ስሌት ኢትዮጵያ በጥቅሟ ላይ እንድትደራደርና አሳልፋ እንድትሰጥ ለማድረግ የተደረገውን ጥረት በጽኑ አውግዟል።
የፕሬዚዳንት ትራምፕ ሃላፊነት የጎደለውና ዘመኑን የማይመጥን ንግግር ውድቅ ሃሳብ ሆኖ እንዳገኘውም ገልጿል።
“ግድቡን ግብጽ በቦምብ ትደረምሰዋለች የሚለው እብሪት የተጫነው ንግግር በኢትዮጵያ ላይ የጦርነት አዋጅ ከማወጅ የማይተናነስ በመሆኑ ሁሉም ለፍትህ የቆሙ ወገኖች ሊያወግዙት ይገባል’’ ብሏል።
አድሏዊነትና ኢፍትሃዊነት አሰራር በሁሉም ሃይማኖቶች የሚወገዝ መሆኑን አመልክቶ፤ “እኔ ብቻ ልብላ የሚል ግለኛ አመለካከት በምንም መልኩ ተቀባይነት የለውም” ሲል የፕሬዚዳንቱን ንግግር ኮንኗል።
“አገራዊ ሃብታችንን የመጠቀም መብትን ለመከልከል የተነሳውን የውጭ ሃይል በጋራ በመሆን ልንመክተው ይገባል” ያለው የጉባኤው መግለጫ፤ በዚህ ረገድ የተጋረጡ ፈተናዎችን በአስተውሎትና በጥበብ ማለፍ እንደሚገባ በመግለጽ ጥሪ አቅርቧል።
( ኢዜአ)

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.