የአሜሪካው ፕሬዝዳንት በአገራችን ላይ ያስተላለፉት የጦርነት ጥሪ እንቃወማለን- ቅዱስ ሲኖዶስ - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት በአገራችን ላይ ያስተላለፉት የጦርነት ጥሪ እንቃወማለን- ቅዱስ ሲኖዶስ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ታላቁን የሕዳሴ ግድብ አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ፣ የአገራችን ሰላምም ሆነ ጥቅም ሊያሳጣ በሚችል መልኩ ጥቅምት 13 ቀን 2013 ዓ.ም የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ያስተላለፉትን የጦርነት ጥሪ አውግዟል።
በአገራችን ኢትዮጵያ የሕዝባችንን የዘመናት ድህነት እና የኑሮ ጉስቁልና አስወግዶ ለአገራችን ብልጽግና ያመጣል ተብሎ ከፍተኛ ተስፋ የተጣለበትን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሥራው ተጀምሮ በአሁኑ ጊዜ በጥሩ ደረጃ ላይ መድረሱን መግለጫው ጠቅሷል።
የግድቡ የዕለት ከዕለት ሥራ እየተከናወነ ሕዝባችንም የተለመደ ድጋፉን እያደረገ ከሦስት ዓመታት በኋላ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ እንደሚደርስ ተስፋ የተጣለበት መሆኑንም ጠቁሟል።
ይሁን እንጂ ሕዝባችን በዚህ ተስፋ ውስጥ በገንዘቡም በጉልበቱም በሙያውም የበኩሉን ድጋፍ በማበርከት እየተረባረበ ባለበት ወቅት ይህን መሰል ንግግር መምጣቱ እንዳሳዘነው ቅዱስ ሲኖዶስ ገልጿል።
አገራችን ኢትዮጵያ በዘመናት ውስጥ ታፍራ እና ተከብራ የኖረችው እና ለመላው ጥቁር ሕዝብ ምሳሌ የሆነችው አገሪቱ አገረ እግዚአብሔር ሕዝቡ ሕዝበ እግዚአብሔር በመሆኑ ነው ብሏል።
ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕም ሆነ ከሌሎች ተመሳሳይ አካላት በአገራችን ላይ እየተላለፈ ያለው የጥፋት ጥሪ መተዛዘቢያ ከሚሆን በስተቀር የአገራችን ጠባቂዋ በሆነው እግዚአብሔር እና በሕዝባችን አንድነት ተከብራ እና ተጠብቃ እንደምትኖር ሙሉ እምነታችን ነው ሲል ገልጿል።
መላው የዓለም መንግሥታት እና ሕብረተሰብ ችግሩን በጥልቀት እንዲገነዘቡትም ጠይቋል።
በአገር ውስጥ ሆነ ከአገር ውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን፣ የፌዴራል እና የክልል መሪዎች፣ ተፎካካሪ ፓርቲዎችም የትኛውንም የግል እና የቡድን አመለካከት ወደ ጐን በመተው አንድነታቸውን በማጠናከር ለአገራችን ሕልውና እንዲቆሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪ አቅርቧል።

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.