ታላቁ የህዳሴ ግድብን ከፍፃሜ ከማድረስ ለአፍታም ያህል የሚያቆመን አይኖርም- የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

ታላቁ የህዳሴ ግድብን ከፍፃሜ ከማድረስ ለአፍታም ያህል የሚያቆመን አይኖርም- የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

ታላቁ የህዳሴ ግድባችንን ከፍፃሜ ከማድረስ ለአፍታም ያህል የሚያቆመን ገቢር አይኖርም አለ የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት።
ምክር ቤቱ ባወጣው መግለጫው፥የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራንፕ ግድቡን አስመልክተው ያስተላለፉት መልእክት ኃላፊነት የጎደለው የአሜሪካ መንግስትንም ሆነ ህዝብ የማይመጥን ነውብሏል።
እንዲህ አይነቱ ኃላፊነት የጎደለው እና የማንአለብኝነት አነጋገር ከአንድ ለዴሞክራሲ፣ ለእኩልነት እና ለፍትህ እቆማለሁ ከምትል አገር ፕሬዚዳንት ሲሰማ ደግሞ እጅግ አሳዛኝና አሳፋሪ ሆኖ እናገኘዋለን ብሏል ምክር ቤቱ።
በእርግጥ የፕሬዚዳንት ትራንፕ ንግግር ከግል ስሜት የመነጨ የግል ፍላጎት የሚያንፀባርቅ እንጂ በማንኛውም መልኩ የአሜሪካን ህዝብንም ሆነ ምክር ቤቶች የማይወክል እንደሆነም እንደሚያምን አስታውቋል።
የኢትዮጵያና የአሜሪካ ህዝብ የረዥም ግዜ ጥሩ ወዳጅ ህዝቦች ናቸው ያለው ምክር ቤተ፥ እንዲሁም የኢትዮጵያና የአሜሪካ መንግሥታት ጠንካራ ስትራቴጂካዊ ትብብር እና ወዳጅነት ያላቸው መንግስታት ናቸው፤ ይህ ግንኙነትና ትብብር ወደፊትም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብሏል።
ለእኛ ለኢትዮጵያዊያን የህዳሴው ግድባችን የማንነታችን አርማ፣ የንድነታችን መገለጫ እና የቃል ኪዳናችን ህያው ሐውልት ነውሲልም አስታውቋል።
በሳለፍነው የጋራ ታሪካችን የቀኝ ገዢዎችን ፍላጎትና በተደጋጋሚ ከውጭ ወራሪ ኃይሎች የተቃጣን የወረራ ጥቃት በአንድነትና በተባበረ ክንድ እንዳከሸፍን ሁሉ፤ ከውስጥ እና ከውጭ በየጊዜዉ የሚያጋጥሙን ጥቃቶችና ሴራዎች እንደወትሮው ሁሉ በአንድነት ተቋቁመንና መክተን ታላቁን የህዳሴ ግድባችንን ከፍፃሜ ማድረስ ይኖርብናል ብሏል ምክር ቤቱ በመግለጫው።
እኛ ኢትዮጵያዊያን በአሁኑ ወቅት ከምንጊዜውም በላይ በአንድነት ልንቆም ይገባልያለው ምክር ቤቱ፥በአንድነት መቆም ምርጫ አይደለም ግዴታ ነው፤ የህልውና የሉዓላዊነት ጉዳይ ነውሲልም አስታውቋል።
ኤፍ..

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.