የህዳሴ ግድብ ሱዳንን ከጎርፍ ጥፋት ይታደጋል—ኢንጂነር ስለሺ በቀለ - መነሻ - am
Nested Portlets
Asset Publisher
Statistics
Web Content Search
Asset Publisher
የህዳሴ ግድብ ሱዳንን ከጎርፍ ጥፋት ይታደጋል—ኢንጂነር ስለሺ በቀለ
ሚኒስትሩ ትናንት በሰጡት መግለጫ በሱዳን በጎርፍ ምክኒያት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች ሲያወድሙ በአስር ሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ደግሞ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል ብለዋል፡፡
በዘንድሮ አመት የህዳሴ ግድብ ውሃ ባይዝ ኖሮ ችግሩ የከፋ ይሆን እንደነበር ኢንጂነር ስለሺ ተናግረዋል።
እንደሚኒስትሩ ገለጻ ኢትዮጵያ በአባይ ላይ የምትገነባው የህዳሴ ግድብ በታችኞቹ የተፋሰስ ሃገራት የጎርፍ አደጋውን በመቀነስ ረገድ ትልቅ አስተዋጽዖ አበርክቷል።
የቀጠናው ሀገራት የጎርፍ መጥለቅለቅንና ድርቅን በማስተዳደርና ውሃ በማቅረብ ከሚገኙ ጥቅሞች በተጨማሪ የታዳሽ ኃይልን ለማዳበር የህዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለውም አክለዋል፡፡
በመስከረም ወር አጋማሽ ላይ የሱዳን ሲቪል መከላከያ 121 ሰዎች በጎርፍ አደጋው መሞታቸውን አስታውቆ እንደነበር ይታወሳል።
ሲቪል መከላከያው በሀገሪቱ በርካታ ግዛቶች በሚገኙ የእርሻ መሬቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዳደረሰ አሎማህ ዶት ኮም (ALOMAH.COM) አመልክቷል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ባለፈው ወር ለተመድ ባደረጉት ንግግር «እኛ ሱዳንንም ሆነ ግብጽን የመጉዳት ፍላጎት የለንም» ይልቅስ ግድቡ በሁሉም ዘርፍ ለሁላችን ጠቃሚ ነው ማለታቸው ይታወሳል።
ግድቡ ለሶስቱ ሃገራት ግጭት ምንጭ ሊሆን እንደማይገባም ማስገንዘባቸው ይታወሳል።
ግድቡ ሲጠናቀቅ ለ 65 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የኤሌክትሪክ ኃይል ይሰጣል ፡፡