የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እና ሌሎች ግድቦች በደለል እንዳይሞሉ ጠንካራ የደን ልማት ስራ ሊካሄድ ይገባል- ምሁራን - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እና ሌሎች ግድቦች በደለል እንዳይሞሉ ጠንካራ የደን ልማት ስራ ሊካሄድ ይገባል- ምሁራን

አዲስ አበባ  ሀምሌ 2  2012 (ኤፍ..)የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እና ሌሎች በኢትዮጵያ የሚገኙ ግድቦች በደለል እንዳይሞሉ የወንዞች መነሻ በሆኑ ተራራማ አካባቢዎች ጠንካራ የደን ልማት ስራ ሊካሄድ  እንደሚገባ ምሁራን ተናገሩ።

በዘርፉ ላይ በርካታ ጥናት ያካሄዱት  ፕሮፌሰር በላይ ስማኔ እና ዶክተር ውባለም ታደሰ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ ÷ግድቦችን ከመገንባት ጎን ለጎን የአረንጓዴ አሻራ እንቅስቃሴው በጠንካራ ተቋማት ሊደገፍ ይገባል ብለዋል 

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ  የሀገር ልማት እና ጥናት ትምህርት ክፍል መምህር እና ተመራማሪው ፕሮፌሰር በላይ ስማኔ  የዓባይ ወንዝ ተፋሰስ በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳት እየደረሰበት መሆኑን  ተናግረዋል 

ፕሮፌሰር በላይ የታችኛው ተፋሰስ አባል ሀገራት በዚህ ጉዳይ ላይ ትኩረት አለማስጠታቸው አስገራሚ  እንደሆነም አብራርተዋል።

ዓባይ  እንክብካቤ ከተደረገለት ለሁሉም የሚበቃ ታላቅ ወንዝ ነው ፣የተፋሰሱን ምህዳር በዘላቂነት ለመንከባከብ እንቅስቃሴ መደረግ አለበትም ነው ያሉት

በደን ልማት ዙርያ ካለፉት 20 ዓመታት ጀምሮ ጥናት እና ምርምር እያደረጉ የሚገኙት ዶክተር ውባለም ታደሰ በበኩላቸው የአረንጓዴ አሻራውን የችግኝ ተከላ ፕሮግራሙ  ከግድቦቻችን እኩል ትኩረት ሊሰጠው ይገባል  ብለዋል 

ዶክተር ውባለም አያይዘውም ዘላቂ የሆነ እና በተጠና መንግድ የደን ልማት ካልተካሄደ ፣የተራቆቱ ተራሮች አረንጓዴ ካለበሱ የሚገነቡ ግድቦች በደለል መሞላታቸው አይቀሬ  ነው ብለዋል።

ምሁራኑ አክለውም በዘርፉ ላይ ሩቅ ሳንሄድ የተሻለ ውጤት ካስመዘገቡት አፍሪካዊያን ወንድሞቻችን ሯዋንዳ እና ጋና ልምድ ልንቀስም ይገባልም ነው ያሉት።

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.