በህዳሴ ግድብ ላይ የኢትዮጵያን መብት በተመለከተ ለዓለም ግንዛቤ ለመፍጠር የሚያስችል የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ተጀመረ - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

በህዳሴ ግድብ ላይ የኢትዮጵያን መብት በተመለከተ ለዓለም ግንዛቤ ለመፍጠር የሚያስችል የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያውያን በህዳሴ ግድብ ላይ የኢትዮጵያን መብት በተመለከተ ለዓለም ግንዛቤ ለመፍጠር የአምስት ቀናት የማህበራዊ ሚዲያ (ኦንላይን) ዘመቻ ጀምረዋል፡፡

አባይ ለኢትዮጵያ በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ዘመቻ ለአምስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን እስከ ፊታችን ዓርብ ድረስ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

በዘመቻው ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ግድብ ላይ ያላትን መብት በተመለከተ የማስገንዘብ ስራ ይሰራል፡፡

ከዚህ ባለፈም ግብጽ በህዳሴው ግድብ ላይ የምትነዛውን አሳሳች ትርክት ለመመከት ያለመ ነው፡፡

በተለይም በትዊተር ላይ እየተካሄደ ባለው ዘመቻ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ምንም ዓይነት ልዩነት ሳይገድባቸው ስለ አባይ እና የህዳሴ ግድብን በተመለከተ መረጃዎችን እያሰራጩ ይገኛሉ፡፡

በርካቶችም ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ ስላላት መብት ጥብቅና በመቆም መረጃወችን ለቀረው ዓለም እያደረሱ ነው፡፡

ኢትዮጵያ የናይል ወንዝ 86 በመቶ ምንጭ ሆና ሳለ እና መቶ በመቶ በራሷ ወጪ የህዳሴ ግድብን እየገነባች ቢሆንም ለወንዙ ምንም አይነት ውሃ ከማታዋጣው ግብጽ ጋር ግን በጋራ ጥቅም በማመን ለረጅም አመታት ድርድሮችን ስታደርግ ቆይታለች፡፡

ግብጽም ኢትዮጵያውያን በአባይ ወንዝ ላይ ምንም አይነት ግድብ ለመገንባት አቅም እንዳይኖራቸው ለዘመናት ብዙ መጣሯም የሚታወቅ ነው፡፡
በጥቅሉም ግብጾች ኢትዮጵያን የማዳከምና ገጽታዋን የማጠልሸት ዘላቂ ግብ በመያዝ በመስራት ላይም ይገኛሉ፡፡

ኢትዮጵያውያኑም ከራሳችን ከሚመነጭ ውሃና ከራሳችን በተዋጣ ገንዘብ የምንገነባው የህዳሴ ግድብ ግንባታውም ሆነ አፈጸጻሙ ለሌላ ፈቃጅና ከልካይ ፍላጎት የሚተው አይደለም በሚል ኢትዮጵያ የያዘችውን ፍትሃዊ አቋም በእነዚህ ቀናት የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻዎች ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ግንዛቤ በመፍጠር ላይ ይገኛሉ፡፡

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.