ኤግዚቢሺኑ በውሃና ኢነርጂ ዘርፍ የተሰሩ ስራዎች አፈጻጸም ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን እንድናይ አድርጎናል - አስተያየት ሰጭዎች - መነሻ - am
Nested Portlets
Asset Publisher
Statistics
Web Content Search
Asset Publisher
የዉሃና ኢነርጂ ኤግዚቢሺን ከታዳጊ ሕፃናት እስከ አረጋውያን ሁሉምን የማህበረሰብ ክፍል ባሳተፈ መልኩ በየእለቱ በግልና በቡድን እየተጎበኘ ይገኛል፡፡
በዛሬው ዕለት ኤግዚቢሺኑን ሲጎበኙ አግኝተናቸው የነጋገርናቸው አስተያየት ሰጭዎች የሚከተለውን ብለውናል፡፡
የመጀመሪያ አስተያየት ሰጭ የሆነችው ኤልዳና ብርሃኑ በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳደር ኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ቱሉ ዲሚቱ ወረዳ የሴቶች ሊግ አመራር መሆኗን ገልጻልናለች፡፡
ኤግዚቢሺኑን እንዴት አገኘሽው ብለን የጠየቅናት ሲሆን እጅግ ከጠበቀችው በላይ በርካታ ክንውኖች የቀረቡበት እንደሆነና ከበቂ በላይ ግንዛቤ ያገኘችበት ስለመሆኑ ተናግራለች፡፡
እንደ ኤልዳና አስተያየት በተለይም የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሂደት አሰመልክቶ የተደረገላት ገለጻ ስለግድቡ አጠቃላይ ሂደት በዝርዝር የተበራራላትና ከዚህ ቀደም በቂ ግንዛቤ ያልነበራት መሆኑን ጠቅሳ አሁን ግን በቂ ግንዛቤ ማግኘቷን ተናግራለች፡፡
የተሻል ግንዛቤ በማግኘቷም ለቀሪ የግድቡ ስራዎች በሚደረጉ ድጋፎች ሌሎችንም በማሰተባበር የበኩሏን እንደምትወጣ ግልጻልናለች፡፡
ሌላዋ አስተያየት ሰጭያችን ደግሞ ሰሚራ አብዱልጀሊል ተባላለች የመጣቸው ከኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳደር ኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ቱሉ ዲሚቱ ወረዳ ሲሆን ከኤግዚቢሺኑ በቂ ግንዛቤ ማግኘቷንና ከዚህ በፊት በታላቁ ህዳሴ ግንባታ ምንም አይነት አስተዋጽኦ ያላደረገች መሆኑን ጠቅሳ በወረዳው ባሉ የበጎ አድራጎት አደረጃጀቶች ከታቀፈች በኋላ ግን ወጣቶችን በማስተባበር ሌሎችም ለግድቡ ግንባታ ድጋፍ እንዲያደርጉ በማነሳሳት ላይ መሆኗን ተናግራለች፡፡
አሁን በተጨባጭ እየታየ እናዳለው ቀጣዩ ትውል ብሩህ ጊዜ እየመጣለት እንዳለ እረዳለው መንግስት የልማት ስራዎቹን አጠናክሮ ይቀጥል እኛም ከጎኑ ነን ብላለች፡፡