ታላቁ የህዳሴ ግድብ ብሄራዊ ምልክታችን ነው - በሽገር ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ጽ/ቤት ልዩ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ ኡርጌ - መነሻ - am
Nested Portlets
Asset Publisher
Statistics
Web Content Search
Asset Publisher
በዛሬው የውሃና ኢነርጂ ዘርፍ ኤግዚቢሺን ጉብኝት በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሸገር ከተማ አስተዳደር አስተባባሪነት ከቡራዩ፣ መልካኖኖ፣ ገፈርሳጎጄ፣ ሱሉልታ፣ መና አቢቹ እና ኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተሞች የተወጣጡ ከ5,000 በላይ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል፡፡
እንደ ከተማ አስተዳደሩ ከ10,000 በላይ ጎብኝዎችን በኤግዚቢሺኑ ለማሰተፍ ታስቦ በዛሬው ዕለት ከ6 ክፍለ ከተማዎች ከ5,000 በላይ የማህበረሰብ ክፍሎችን ማሳተፍ መቻሉንና በነገው ዕለት 6 ክፍለ ከተሞች የተወጣጡ ከ5,000 በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ኤግዚቢሺኑን እንደሚጎበኙት በሽገር ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ጽ/ት ቤት ልዩ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ ኡርጌ ተናግረዋል፡፡
አቶ ግርማ በኤግዚቢሺኑ በግላቸው ስለተገነዘቡት ጉዳይ ሲጠቅሱ በውሃና ኢነርጂ ዘርፍ እንደ ሀገር በርካታ ስራዎች መሰራታቸውንና አሁን በረካታ ተግባራት እየተከናወኑ ስለመሆኑ መረዳት ችያለው ብለዋል፡፡
አቶ ግርማ አክለው ሲገልጹም በተለይ በእኛ በኢትዮጵያዊያን አቅም እየተገነባ ያለውና ብሄራዊ ምልክታችን የሆነው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ከ91 በመቶ በላይ መድረሱንና እስከ አሁን በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ በቂ ገለጻ በመደረጉ በግሌ እጅግ ተደስቻለው ብለዋል፡፡
ለግድቡ ቀሪ ስራዎች እንደ ከተማ አስተዳደሩ የሚጠበቅብንን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነን ያሉት አቶ ግርማ እሰከ አሁን ድረስ በቦንድ ግዥ፣ በገንዘብ ልገሰና ለግድቡ ያልን ድጋፍ በማሳየት የበኩላችንን አስተዋጽኦ እያደረግን እንገኛለን ብለዋል፡፡