የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ለወጣቱ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው ተገለጸ - መነሻ - am
Nested Portlets
Asset Publisher
Statistics
× አድራሻ: ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስኩየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር
Web Content Search
Asset Publisher
በብሄራዊ ሳይንስ ሙዚየም ለዕይታ ክፍት የሆነው የውሃና ኢነርጂ ኤግዚቢሺን በርካቶች በግልም ሆነ በቡድን እየጎበኙት ይገኛሉ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ልደታ ክፍለ ከተማ አስተባበሪነት በክፍለ ከተማው ከሚገኙ 10ም ወረዳዎች የተወጣጡ ከ300 በላይ ወጣቶች የውሃና ኢነርጂ ኤግዚቢሺንን በዛሬው ዕለት ጎብኝተዋል፡፡
ታዲያ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆነውና በኤግዚቢሺኑ ጉብኝት ሲሳተፍ ያገኘነው ወጣት ያሬድ ግርማቸው ኤግዚቢሺኑ ለወጣቱ ስላለው ጠቀሜታና በግሉ ስላገኘው ግንዛቤ አብራርቷል፡፡
እንደ ወጣት ያሬድ ግርማቸው ገለጻ ወጣቶች በተለያዩ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ዘርፎች በንቃት በመሳተፍ ግንባር ቀደም ሚናቸዉን ሊጫወቱ ይገባል፡፡
በተለይ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ለወጣቱ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ ለግድቡ ግንባታ መጠናቀቅ ወጣቶች በቀሪ ጊዜያት በንቅናቄ ስራዎች፣ ለግድቡ ግንባታ የሚውል የገንዘብ ልገሳ፣ የቦንድ ግዥ እንዲሁም በአከባቢ ጥበቃና ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ተግባራት በንቃት መሳተፍ ይገባቸዋል ብሏል፡፡
Nested Portlets
Asset Publisher
መጣጥፎች
— 5 Items per Page