በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አፈጻፈም ተደስተናል - የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮች - መነሻ - am
Nested Portlets
Asset Publisher
Statistics
× አድራሻ: ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስኩየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር
Web Content Search
Asset Publisher
በምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ነብዩ ዳኜ የተመሩት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ከፍተኛ የአመራር አካላት በሳይንስ ሙዚየም የተሰናዳውን የውሃና ኢነርጂ ኤግዚቢሺን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን ኢትዮጵያ በዘርፉ የደረሰችበት ደረጃ አስደናቂ ነው ብለዋል፡፡
በጉብኝቱም የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አፈጻፈም፣ ከመነሻው ጀምሮ አሁን ግድቡ ስከደረሰበት ደረጃ ያለው የመሪዎች ቅብብሎሽ፣ የኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሁለንተናዊ ድጋፍና ተሳትፎ እንዲሁም የሃብት አስባሰብ ተግባራትና በቀጣይ ሰልሚያስፈልጉ የድጋፍ አይነቶች ማብራርያ የተሰጠ ሲሆን የግድቡ ግንባታ አሁን ስለደረሰበት ደረጃም ሰፋ ያለ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡
በጉብኝቱ የተሳተፉ የአመራር አካላት በተደረገላቸው ገለጽ በጣም የተደሰቱ መሆኑንና የግድቡ ግንባታ ወደ መጠናቀቁ በመድረሱ እጅግ መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም እንደ ኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ለቀሪ ስራዎች የሚጠበቅብንን ሁሉ ለማድረግም ዝግጁ ነን በማለትም ተናግረዋል፡፡
Nested Portlets
Asset Publisher
መጣጥፎች
— 5 Items per Page