ከታላቁ ኅዳሴ ግድብ ኃይል ለማመንጨት ዝግጅቱ እየተገባደደ ነው - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

ከታላቁ ኅዳሴ ግድብ ኃይል ለማመንጨት ዝግጅቱ እየተገባደደ ነው

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ግንባታ የመጀመሪያ ዙር ኃይል ማመንጨት በሚያስችል ደረጃ እየተገባደደ መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ (/) ለዋልታ ገለፁ፡፡

ግድቡ ተጠናቆ ለታለመለት ዓላማ እንዳይውል የሚሹ የውጭ ኃይሎች ተላላኪያቸው የሆነውን አሸባሪው ትሕነግ በመጠቀም ለማደናቀፍ ቢጥሩም በመላው ኢትዮጵያዊያን ቁርጠኝነት የታላቁ ኅዳሴ ግድብ ግንባታ ወደ መጠናቀቁ ምዕራፍ እየሄደ መሆኑን አሳውቀዋል፡፡

በኢትዮጵያ ላይ እየደረሰ ያለው ጫና መላው ኢትዮጵዊያንን ቁጭት ውስጥ የከተተ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ሀብታሙ (/) የኅዳሴ ግድቡ ግንባታ ላይ የሚሰሩ ኢትዮጵያዊያንም በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ውስጥ ሆነው በከፍተኛ ወኔና በቁጭት 24 ሰዓት እየሰሩ ነው ብለዋል፡፡

ጠላትን ማሸነፍ የሚቻለው በጦር ግንባር ብቻ አይደለም ያሉት ሚኒስትሩ የልማት ሥራዎችን በተገቢው መንገድ በማጠናቀቅና የአገሪቱን ብልጽግና በማረጋገጥ ድልን መጎናፀፍ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ሚኒስትሩ ከዋልታ ጋር ባደረጉት ቆይታ መላውኢትዮጵያዊያን ለግድቡ ግንባታ የሚችሉትን ሁሉ ድጋፍ እያደረጉ ነው ያሉም ሲሆን አሁንም የሚደረገውን ድጋፍ በማጠናከር ግድቡ ተጠናቆ የሚሰጠውን የኃይል ጥቅም መቋደስ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

(ዋልታኅዳር 27/2014

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.