መልካም አዲስ ዓመት! ለመላው ኢትዮጵያውያን - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

መልካም አዲስ ዓመት! ለመላው ኢትዮጵያውያን

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ፅ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሄ ለመላው ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ሁሉ የመልካም አዲስ ዓመት መልዕክት ከግድቡ ግንባታ ስፍራ አስተላለፉ።  " ዋና ዳይሬክተሩ በመልዕክታቸው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አሁን ለደረሰበት ከፍተኛ የግንባታ ደረጃ የደረሰው ኢትዮጵያውያን አንድነታችንን አጠናክረን በዕውቀት፣ በጉልበት ፣ በገንዘብ እና በህዝብ ዲፕሎማሲ ተረባርበን በመስራታችን ነው።  ባለፉት አስር ዓመታት በተለይም ዘንድሮ 2013 ዓ/ም በርካታ ተፈጥሮአዊ እና ሰው ሰራሽ ፈተናዎችን  አልፈን እዚህ ደርሰናል። እነዚህ ፈተናዎች በአዲሱ ዓመት እንደማይገጥሙን ተስፋ እያደረኩ የበለጠ ተቀናጅተን በአንድነት ከቆምን ምንም ዓይነት ፈተናዎችን አልፈን የሀገራችንን ሰላም፣ አንድነት እና ብልፅግና እናረጋግጣለን!" ብለዋል። ዋና ዳይሬክተሩ የግድቡን ግንባታ የጎበኙ ሲሆን በግንባታ ላይ የሚገኙትን ሰራተኞች  " እናንተ ዛሬ በዚህ ግንባታ ላይ የምትገኙ የኢትዮጵያ አብራክ ያፈራቻችሁ የቁርጥ ቀን ጀግኖች ናችሁ፣ ኢትዮጵያ ትኮራባችኃለች ሁል ጊዜም በታሪክ ትታወሳላችሁ!" ሲሉ በማነቃቃት እና በማበረታታት:ምስጋናም አቅርበዋል። በመልዕክታቸውም ለሁሉም ኢትዮጵያውያን አዲሱ ዓመት (2014ዓም ) የሰላም ፣የጤና፣ የፍቅር እና አንድነት እንዲሆን በመመኘት እንኳን አደረሳችሁ ሲሉ በሃገሪቱ ጥፋት ላይ ለተሰማሩ ኃይሎች ልብ እንዲገዙ እና እንዲመለሱ ካልሆነ ግን ከመላው ኢትዮጵያውያን ክንድ እንደማያመልጡ አስጠንቅቀዋል? በተጨማሪም የኢትዮጵያን ሰላም እና አንድነት ለማስከበር በሀገራዊ ተልዕኮ በመፋለም ላይ ላሉ የመከላከያ ሰራዊታችን፣ የፖሊስ ኃይሎች፣ ልዩ ኃይል እና ሚሊሺያ እንኳን አደረሳችሁ በማለት አዲሱ ዓመት የድል እና የሰላም እንደሚሆን ገልፀው መላው ህዝባችን ከሰላም ኃይሉ ጎን በመቆም ለሃገሩ የሚጠበቅበትን ሁሉ እንዲወጣ በማለት በታላቁ  ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ም/ቤት ጽ/ቤት እና በራሳቸው  ስም ጥሪ በማድረግ የዘመን መለወጫ ባህሉ የሰላም እና የጤና እንዲሆንም ተመኝተዋል።                                                          

ጳጉሜ 5/2013 ዓ/ም

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.