የፅናት እና የመቻል ብሔራዊ ማህተማችን የሆነው የህዳሴ ግድባችንን ለታቀደለትና ለዘላቂ አገራዊ ፍላጎታችን ማረጋገጫነት ለማዋል የሚደረገው ርብርብ ተጠናክሮ ቀጥሏል - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

የፅናት እና የመቻል ብሔራዊ ማህተማችን የሆነው የህዳሴ ግድባችንን ለታቀደለትና ለዘላቂ አገራዊ ፍላጎታችን ማረጋገጫነት ለማዋል የሚደረገው ርብርብ ተጠናክሮ ቀጥሏል

በብሔራዊ ጥቅማችን ፣ አንድነትና ደህንነታችን ጉዳይ ላይ የማይነቀነቅ መሰረት የመጣል ቁርጠኝነታችን በላቀ ህዝባዊ ተሳትፎ ያረጋገጥንበት የፅናት እና የመቻል ብሔራዊ ማህተማችን የሆነው የህዳሴ ግድባችንን ለታቀደለትና ለዘላቂ አገራዊ ፍላጎታችን ማረጋገጫነት ለማዋል የሚደረገው ርብርብ ተጠናክሮ መቀጠሉን የኢትዮጵያ የኤልክትሪክ ሀይል ቦርድ ሰብሳቢና የሳይንስ፣ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ ገለጹ፡፡
በሚኒስትሩ የተመራ ልዑክ ታላቁ ህዳሴ ግድብ የደረሰበትን ደረጃ ቦታው ድርስ በመሄድ የመስክ ጉብኝት አድርጓል።
ዶክተር አብርሃም በላይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው “ብዙ ፈተናዎችና የተለዮ ጫናዎችን በመቋቋም ጭምር ወደ ፊት የሚገሰግሰው የኢትዮጵያችን ንጋት ጉዳይ ለአይን ሽፋሽፍቶቻቸው እንቅልፍ የማይሰጡ ንቁ ንስር አይኖችንና የማይዝሉ ጠንካራ ክንዶችን አስተባብሮ ቀጥሏል” ሲሉ ገልጸዋል።
“በሶስት አመት ፈታኝ የአገራዊ ለውጥ ጉዞአችን ውስጥ ባለሰንደቅ ንኡስ ክንዋኔዎች (Flagship Milestones) ውስጥ በቅርቡ የተከናወነው ሁለተኛው ዙር የውሀ ሙሌትና ያለ አግባብ በአለም አቀፍ መድረክ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ጠረጴዛ ቀርቦ በተገቢው አሁጉራዊ መድረኩ እንዲታይ ውሳኔ የተሰጠበት ድላችን አንፀባራቂ ውጤቶቻችን ናቸው” ሲሉም ገልጸዋል።
በብሔራዊ ጥቅማችን ፣ አንድነትና ደህንነታችን ጉዳይ ላይ የማይነቀነቅ መሰረት የመጣል ቁርጠኝነታችን በላቀ ህዝባዊ ተሳትፎ ያረጋገጥንበት የፅናት እና የመቻል ብሔራዊ ማህተማችን የሆነው የህዳሴ ግድባችንን ለታቀደለትና ለዘላቂ አገራዊ ፍላጎታችን ማረጋገጫነት ለማዋል የሚደረገው ርብርብ ተጠናክሮ መቀጠሉን በመስክ ጉብኝት ወቅት ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል።
“በአለም አቀፍ ህግጋት ተገዢነትና በጋራና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት እሳቤ የተቃኘው አገራዊ አቋማችን ዉሎ አድሮ በተግባር የህዝቦች የወንድማማችነት ግንኙነትን የሚያጠናክር የተስፋ ጎህ ይዞ እንደሚቀድ አይኖች ይመለከታሉ” ሲሉም ነው የገለጹት።

10/12/13
ምንጭ፡- ኢዜአ

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.