በኒውዮርክ እና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለታላቁ የህዳሴ ግድብ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸው ተገለፀ፡፡ - መነሻ - am
Nested Portlets
Asset Publisher
Statistics
Web Content Search
Asset Publisher
የገንዘብ ድጋፉ የተደረገው በትራይስቴት፣ በኒውዮርክ፣ በኒውጀርሲ፣ ኬነቲኬት እንዲሁም በሌሎች ስቴቶች ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር በዌብናር በተደረገ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር ፕሮግራም ላይ ነው፡፡
በውይይቱ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢ.ፌ.ድ.ሪ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን÷ የህዳሴው ግድብ ድርድር ሁለት ጊዜ በተ.መ.ድ. የፀጥታው ምክርቤት የቀረበበት አግባብና ጉዳዩ በአፍሪካ መድረክ እንዲታይ የተደረገውን ብርቱ ትግልና ቀሪ ጉዳዮችን እንዲሁም እስካሁን የተመዘገበው ድል የሁሉም ጥረትና ተቀናጅቶ የመስራት ውጤት መሆኑን በንግግራቸው ጠቅሰዋል።
ኢንጂነር ጌዲዮን አስፋው በበኩላቸው÷ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የደረሰበትን ደረጃና የድርድሩ ሂደትን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ በተለይም በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የሚቀርቡትን የተሳሳቱ አመለካከቶች እና እንቅስቃሴዎች መመከት ያስፈልጋል ብለዋል።
አርቲስት ደበበ እሸቱ ሀገራችን ላይ በአሁኑ ጊዜ የሚታየው ችግር መነሻው ከአባይ ውሀ ጋር የተያያዘ ሲሆን÷ መፍትሄው ሁላችንም ከምንጊዜው በላይ ተደጋግፈን ልንቆም ይገባል ብለዋል።
ተሳታፊዎችም በቀረበላቸው ገለፃ÷ ደስተኛ መሆናቸውን በመግለጽ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል ከ62ሺህ ዶላር በላይ የገንዘብ ስጦታ ለግሰዋል።
ለወደፊቱም የታላቁን የህዳሴ ግድብ ግንባታ እስከሚጠናቀቅ የበኩላቸውን የፋይናንስ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል መግታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት ያኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኤፍ ቢ ሲ ፣ ነሃሴ 6፣ 2013 ዓ.ም