‹‹የታላቁ ህዳሴ ግድብ የአፍሪካን በራስ የመልማትአቅም ማሳያ ነው››አቅም ማሳያ ነው›› ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

‹‹የታላቁ ህዳሴ ግድብ የአፍሪካን በራስ የመልማትአቅም ማሳያ ነው››አቅም ማሳያ ነው›› ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር

የአድዋ ድል ከቅኝ ግዛት ለመላቀቅ መሰረት እንደጣለ ሁሉ የታላቁ ህዳሴ ግድብም የአፍሪካን በራስ የመልማት አቅም የሚያሳይ ጠንካራ አቋም ማሳያ መሆኑን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ አስታወቁ ፡፡
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ኢትዮጵያውያን ለግድቡ እያደረጉት ስላለው ተሳትፎ አስመልክቶ ትናንት በተሰጠው መግለጫ ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ እንደገለጹት፤ የአድዋ ድል ቅኝ ግዛትን ለማሸነፍ መሰረት እንደጣለ ሁሉ የታላቁ ህዳሴ ግድብም የአፍሪካን በራስ የመልማት አቅም ያሳያል፡፡
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሞዴል ሆና በራሷ መቆም ስትችል የሚያስተላልፈው መልዕክት ከፍ ያለ በመሆኑ እውነታው የማያስደስታቸው ወገኖችም አሉ ያሉት ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ ፤ የግድቡ ተጽዕኖ ከሱዳንና ግብጽ ጋር ብቻ የተያያዘ ስላልሆነ ዝግጅታችንና አስተሳሰባችን ያንን ሊያሸንፍ በሚችል ደረጃ መሆን ይገባል ብለዋል።
የግድቡን ደህንነት ለመጠበቅና ኢትዮጵያን አረንጓዴ ለማልበስ በዚህ ዓመት ስድስት ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል መታቀዱን ያስታወሱት ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ ፤ እስካሁን ድረስ 75 በመቶ የሚሆነው ችግኝ መተከሉን አስታውቀዋል፡፡
ለግድቡ እየተደረጉ ያሉ ሁለንተናዊ ድጋፎች አበረታች መሆኑን ያስታወቁት ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ ፤ ድጋፉ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሄ በበኩላቸው፤ ታላቁ የህዳሴ ግድብ የሉአላዊነትና የፍትሃዊነት ማሳያ ከጥገኝነት መላቀቂያ ነውዶክተር ግድቡን ከግብ ለማድረስ ድጋፉ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡
ከገንዘቡ ድጋፍ በተጨማሪ መላው ኢትዮጵያዊ ለግድቡ አምባሳደር ሆኖ ያከናወናቸው የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ድጋፎች የተጠነሰሰውን ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ አሻጥሮች ለመበጣጠስ ትልቅ አቅም መፍጠሩንም ጠቁመዋል፡፡
በተበታተነ መልኩ ሲደረግ የነበረውን ድጋፍ ለማሰባሰብና አቅም ለመፍጠር በሥሩ አራት ኮሚቴዎች ያሉት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ትስስር መፈጠሩን ጠቁመው፤ ኢትጵያውያን ይህንን ትስስር በመጠቀም የድርሻቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በዕለቱ ሶስት ድርጅቶች የአራት ሚሊዮን ብር ቦንድ ግዢ የፈጸሙ ሲሆን፤ በ2013 በጀት ዓመት ሁለት ቢሊዮን 49 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን ገልጸዋል፡፡ የግድቡ ግንባታ ከተበሰረ ጊዜ ጀምሮ እስከ ሰኔ 2013 ዓ.ም ድረስ 15 ቢሊዮን 729 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል።
አዲስ ዘመን ሐምሌ 23/2013

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.