የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለታላቁ የሕዳሴ ግድብ ላበረከተው አስተዋጽኦ የእውቅና ሰርተፊኬት ተበረከተለት። - መነሻ - am
Nested Portlets
Asset Publisher
Statistics
× አድራሻ: ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስኩየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር
Web Content Search
Asset Publisher
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ላደረገው አስተዋጽኦ ከሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የእውቅና ሰርተፊኬት ተሰጥቶታል። የእውቅና ሰርተፊኬቱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አማካሪ ዶክተር ፎዚያ አሚን ተረክበዋል።
ሚኒስቴር መስሪያቤቱ እውቅና የተሰጠው ሠራተኞቹን በማስተባበር ካደረገው ድጋፍ ባሻገር በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ በማገዙና የማስተባበሪያ ጽ/ቤቱን ዌብ ሳይትና የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ላይ ባደረገው ከፍተኛ ተሳትፎ ነው።
ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሠራተኞች የብሔራዊ ዳታ ማዕከል አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ መሠረት ንጋቱ እና ወይዘሮ ብዙአየሁ ብርቄ በግል ላደረጉት ሙያዊ አስተዋጽኦ የእውቅናና የምስጋና ሰርቴፊኬት ተበርክቶላቸዋል።
በሚኒስትር ዲኤታ ማዕረግ የሚኒስትሩ አማካሪ ዶክተር ፎዚያ አሚን እንደተናገሩት ማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ ለሰጠው እውቅና አመስግነው በቀጣይ ተቋሙ የሚጠበቅበትን ሁሉ ለማገዝ ከጎናችሁ ይቆማል ብለዋል።
በግል እውቅና ያገኙትን ባለሙያዎች እገዛቸውን አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ያሉት ዶክተር ፎዚያ መሠል እውቅናዎች ሌሎችም ሠራተኞች ከተቋም ተልዕኮ በዘለለ አገራዊ ፕሮጀክቶችን በሙያቸው ለማገዝ የሚያደርጉትን ቁርጠኝነትና መነሳሳት ይጨምራል ብለዋል።
Nested Portlets
Asset Publisher
መጣጥፎች
— 5 Items per Page