“ኢትዮጵያ የተከተለችው ግድቡን እየሰራች የመደራደር ስልት ባለድል አድርጓታል ”አምባሳደር ሽፈራው ጃርሶ - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

“ኢትዮጵያ የተከተለችው ግድቡን እየሰራች የመደራደር ስልት ባለድል አድርጓታል ”አምባሳደር ሽፈራው ጃርሶ


ኢትዮጵያ ግድቡ እንዳይገነባ ለሚጮኹ ድምጾችና ጫናዎች ሳትንበረከክ የተከተለችው እየሰሩ የመደራደር ስልት ባለድል እንዳደረጋት ለረጅም ጊዜ በውሃ ሚኒስትርነት ያገለገሉት አምባሳደር ሽፈራው ጃርሶ አስገነዘቡ፡፡

አምባሳደር ሽፈራው በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፣ ግብፅና ሱዳን የአባይ ወንዝ ከመጠን በላይ ሲሞላ በየዓመቱ ጎርፍ ክፉኛ እንደሚጠቃቸው እያወቁ ፣ በግድቡ መገንባት ለሚቀረው የጎርፍ አደጋ ለኢትዮጵያ መክፈል ሲገባቸው፣ በስልጣን ለመቆየትና የአገራቸውን የፖለቲካ አለመረጋጋት አቅጣጫን ለማስቀየር ግድቡን ቀዳሚ አጀንዳ አድርገው መቅረባቸው የተለመደ ስልት ነው ፡፡

ኢትዮጵያ የተከዜና የጣና በለስ ግድቦች ስትሰራ በነበረው ዓለም አቀፉ ጫናና ማስፈራሪያ ሳትንበረከክ በስኬት ስታጠናቅቅ ጫናዎቹ እንደ ቀነሱ ሁሉ የህዳሴ ግድብም እስክናጠናቅቅ ጫናዎቹ እየበረቱ እንደሚሄዱ ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ ግን ለሱዳንና ግብጽ እንዲሁም ለቀሪው ኃያላን አገራት ዛቻና ማስፈራሪያ ሳትደናገጥ የግንባታው ሥራና የድርድር ሂደቱን ጎን ለጎን በማስኬድ ያደረገችው የሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌቱ ከሁሉም በላይ ድል ያጎናጸፋት ስልት ነው ብለዋል፡፡

የግድቡን ግንባታ ለማስተጓጎል ጠላቶቿ ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም ያሉት አምባሳደር ሽፈራው፣ ኢትዮጵያ 80 በላይ ብሔር ብሔረሰቦች መኖሪያ መሆኗንና ከብረት የጠነከረ አንድነቷን ባለማወቃቸው ሕዝቡን እርስ በርስ በማጋጨት ግንባታውን ለማስተጓጎል የሄዱበት መንገድ ሳይሳካ መቅረቱን አስታውቀዋል ።

የአገሪቱን ሕዝቦች ግድቡ ላባቸው በመሆኑ ከግጭት ይልቅ አንድነት በመምረጣቸው ሴራው ከሽፏል ፣ በግድቡ ላይ ያሰቡት ሴራም ለኢትዮጵያውያን ከፍ ያለ ጥንካሬ መፍጠር ችሏል፤ በግድቡ የተያዘው ውሃ ከአቅማቸው በላይ ስለሆነባቸው ወደኋላ ለመመለስ መገደዳቸውን ጠቁመዋል ፡፡

ከዚህ በኋላ በየትኛው ስሌት የግድቡ ደህንነት ቅንጣት እንደማያሰጋና የውስጥ አንድነት በማጠናከር ከተሰራ ጠላቶቿ የፈሩት የኢትዮጵያ ከፍታ ሩቅ አይሆንም ያሉት አምባሳደሩ፣ ግድቡ ሲጠናቀቅ የአገሪቱን ኢኮኖሚ እድገት በከፍተኛ ሁኔታ ከማፋጠኑ በተጨማሪ ዛሬ ጠላት የሚመስሉ ጎረቤት አገራት ጭምር በኃይል የማስተሳሰርና የማወዳጀት አቅም እንዳለው ገልጸዋል ። ግንባታውን ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ ከወትሮው በበለጠ መረባረብ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡

በተለይ ሱዳን አሁንም ቢሆን የኤሌክትሪክ ኃይል ከኢትዮጵያ እያገኘች፣የግድቡ ግንባታ ከማንም በላይ እንደሚጠቅማት እያወቀች በግብጽ ጉርሻ ተደልላ ከኢትዮጵያ ተቃራኒ መቆሟ የሚያስገርም ነገር ብለዋል።

ያም ሆኖ ግን ኢትዮጵያ ያገኘችውን ድል ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር ስራዋን እየሰራች ከግብጽና ከሱዳን እንዲሁም በግድቡ ግንባታ በተቃራኒ ከተሰለፉ አገራት ጋር ዲፕሎማሲያዊ ድርድሮችን አጠናክራ መቀጠል እንዳለባት አመልክተዋል፡፡

የግድቡ ጉዳይ ለግብጽና ሱዳን የኢኮኖሚ ጉዳይ ሳይሆን የፖለቲካ ጉዳይ መሆኑ ስልጣን ላይ ለመቆየት ዓባይ ሁሌ እንደ አጀንዳ ማቅረብ ግድ እንደሚሆን አመላካች ነው ያሉት አምባሳደር ሽፈራው ፤ ይቅር ዛሬ ግድቡ ሲጠናቀቅም ሱዳንና ግብጽ ስልት በመቀያየር በአገሪቱ ላይ የተለያዩ ሴራዎች ከማሴር ወደኋላ እንደማይሉ ማወቁ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

አዲስ ዘመን ሐምሌ 15/2013

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.