ግብፅና ሱዳን ድርድሩ ከህብረቱ እንዲወጣ የፈለጉት የቅኝ ግዛት ስምምነት ሌጋሲን ለማስቀጠል እንደሆነ ተገለጸ - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

ግብፅና ሱዳን ድርድሩ ከህብረቱ እንዲወጣ የፈለጉት የቅኝ ግዛት ስምምነት ሌጋሲን ለማስቀጠል እንደሆነ ተገለጸ
ግብፅና ሱዳን የግድቡ ድርድር ከአፍሪካ ህብረት ውጭ ባለ አካል እንዲታይ የፈለጉት ስውር እጆችን በማስገባት የቅኝ ግዛት ስምምነት ሌጋሲንን ለማስቀጠል እንደሆነ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፌዴራሊዝምና መልካም አስተዳደር መምህር ዶክተር ተስፋዬ ጂማ ገለፁ።
ዶክተር ተስፋዬ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለፁት፤ ግብፅና ሱዳን የግድቡን ድርድር ከአፍሪካ ህብረት ውጭ ይሁን ማለታቸው እ.ኤ.አ በ1959 የተደረገው ኢ-ፍትሃዊ ስምምነትን ተግባራዊ ለማድረግ በማሰብ ነው።
የህዳሴ ግድቡን ጉዳዩን ግብፅና ሱዳን ከአፍሪካ ህብረት ውጭ ወደ አረብ ሊግና የፀጥታው ምክር ቤት ለመውሰድ መሞከራቸው አንድምታው ከጀርባው የማይታዩ እጆች በጉዳዩ እንዲገቡ በማድረግ የውሳኔ ሂደቱን ለማፋለስ ስለተፈለገ ነው ብለዋል።
የግድቡ ጉዳይ የልማት ወይም የውሃ ጉዳይ በመሆኑ ከአፍሪካ ህብረት አልፎ ወደ ተለያዩ አካላት መቅረብ አልነበረበትም ያሉት ዶክተር ተስፋዬ፤ በሦስተኛ ወገን ይታይ ከተባለ እንኳን በአፍሪካ ህብረት ብቻ ነው መታየት እንዳለበት አስታውቀዋል።
ሁለቱ ሀገራት የህብረቱን የማደራደር ሚና የሚያሳንሱት ጉዳዩን መፍታት ስለማይችል ሳይሆን የቅኝ ግዛት ስምምነት ሌጋሲ ለማስቀጠል በማለም ነው። ሀገራቱ በተደጋጋሚ የሚያነሱት እ.አ.አ የተደረገውን የ1959 ስምምነትን ነው። ይህ ውል በዚያን ዘመን ያስፈፀሙት በተባባሩት መንግሥታት ያሉት አካላት ናቸው። በመሆኑም በማይታይ እጅ የሂደቱ ውሳኔ እንዲሰጥ ይፈለጋል ብለዋል።
እንደርሳቸው ገለጻ፤ ሁለቱ ሀገራት ከድርድሩ የሚሸሹበት ዋናው ምክንያትም ህብረቱ በዚያን ጊዜ የተፈረመውን የቅኝ ግዛት ስምምነት ውድቅ ስለሚያደርግና አዲስ ስምምነት እንዲፈረም ስለሚፈልግ እንደሆነም አስገንዝበዋል።
ሀገራቱ አሁንም በዘመናዊ ቅኝ ግዛት ውስጥ ተይዘው ስለሚገኙ ጉዳዩን ወደ ተባባሩት መንግስታት የሚገፉት መንግስታቱ ጉዳዩን ውድቅ አያደርግም ከሚል እሳቤ የመነጨ ነው። በታቃራኒው ግን የአፍሪካ ህብረት ከተባበሩት መንግስታት በተለየ መልኩ ጉዳዩን በውል ያውቀዋል ብለዋል።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ጉዳይ በአፍሪካ መፈታት አለበት የሚል ፅኑ አቋም ይዛ መቆሟ ለመላው የአፍሪካ ሀገራት ትልቅ ትምህርት ይሆናል ያሉት ዶክተር ተስፋዬ፤ ኢትዮጵያ የወሰደችው ውሳኔ አፍሪካውያን ትንሽ ነገር በተፈጠረ ቁጥር ወደ ምዕራባውያን የሚሮጡበትን ሁኔታ ሊቀንሰው ብሎም ሊያቆመው እንደሚችል እምነታቸውን ገልጸዋል ።
ህብረቱም ለአህጉሩ ህልውና ሲል ጠንከር ብሎ ስራዎችን መስራት እንደሚጠበቅበት ያመለከቱት ዶክተር ተስፋዬ ፣ ሌሎች የአፍሪካ ህብረት ሀገሮችም በትንሽ ነገር በተፈጠረ ቁጥር ወደ ምዕራባዊያን መሮጥ እንደሌለባቸውና የውስጥ ችግራችንን በአፍሪካ መጨረስ እንደሚችሉ በተጨባጭ ማሳየት እንደሚኖርበት ጠቁመዋል።
ግብፅና ሱዳንም ከዚሁ ትልቅ ትምህርት ይወስዳሉ ብዬ አስባለው ያሉት መምህሩ ፣ ህብረቱ ትክክለኛ ስራ ሰርቶ ካሳየ አሁን እንደአጣጠሉት ላይሆን ይችላል፣ እነሱም ወደ ህብረቱ ሊመለሱ ይችላል ብለዋል።
አዲስ ዘመን ሐምሌ 12 ቀን 2013 ዓ.ም

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.