የግድቡ ሁለተኛ ሙሌት የኢትዮጵያን ሁሉን አቀፍ አሸናፊነት እውን ያደረገ ነው - የህግ ምሁራን - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

የግድቡ ሁለተኛ ሙሌት የኢትዮጵያን ሁሉን አቀፍ አሸናፊነት እውን ያደረገ ነው - የህግ ምሁራን

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የግድቡ ሁለተኛ ሙሌት የኢትዮጵያን ሁሉን አቀፍ አሸናፊነት እውን ያደረገ መሆኑን የህግ ምሁራን ገለጹ፡፡

ምሁራኑ ሙሌቱ የመንግስትና የህዝብ መተማመን የሚጨምር፣ የዲፕሎማሲ አሰላለፉን የሚቀይር እና ሀሳብን በእውነት የሚያፀና ነው ብለዋል፡፡

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህሩ ሄኖክ አሻግሬ ግድቡ ሀይል ከማመንጨት በተጨማሪ ራሱን የሚከላከልበት ደረጃ ላይ መድረሱ ሁሉም አሻራቸውን ያስቀመጡ ኢትዮጵያውያን አሸናፊ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል።

ከመረጃ እጥረትና በሀሰት ፕሮፖጋንዳ ከግብፅ ወገን የተሰለፉ ሀገራትም የአሰላለፍ ለውጥ እንዲያደርጉ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ብለዋል ምሁሩ።

ኢትዮጵያ ሙሌቱን ስታካሂድ የታችኞቹ የተፋሰስ ሀገራት ውሃ አለመቀነሱን በማሳያነት ጠቅሰዋል።

በወሎ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህሩ ደጀን የማነ በበኩላቸው ግድቡ ሀይል ለማመንጨት የሚያስችለውን ውሃ መያዙ ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን አመላክተዋል።

ይህም የፍትሃዊ ተጠቃሚነትን መርህ የሚያፀና ብሎም የኢትዮጵውያንን የዘመናት ምኞት ወደ እውነት የቀየረ ብለውታል።

ምሁራኑ ሙሌቱ የህዝቡን ተስፋ የሚጨምር መሆኑን በመጥቀስ እስከ ፍፃሜው ለመትጋት ያስችላል ነው ያሉት።

የግድቡ ግንባታ ሂደት አሁንም የኢትዮጵያውያንን ትብብርና በጋራ መቆምን ይጠይቃል የተባለ ሲሆን በተለይም ዳያስፖራዎች ታሪካዊ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።

በውጭ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በያሉበት ሀገራቸውን በመወከልና የገንዘብ ዝውውር መንገድን ህጋዊ ብቻ በማድረግ በጋራ ሊቆሙ ይገባልም ነው የተባለው።

fbc

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.