ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ የህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር በስኬት በመጠናቀቁ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ - መነሻ - am
Nested Portlets
Asset Publisher
Statistics
× አድራሻ: ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስኩየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር
Web Content Search
Asset Publisher
ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ የህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር በስኬት በመጠናቀቁ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት በመጠናቀቁ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ።
በመልዕክታቸውም "የኢትዮጵያ ሀገራችን ብርቱ ልጆች ያለባቸው ከፍተኛ ውስጣዊ እና ውጫዊ ጫና ሳይበግራቸው ግድባችንን እዚህ ደረጃ ማድረሳቸው እጅግ ያስመሰግናቸዋል" ብለዋል።
በፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ማህበራዊ ትስስር ገጽ ባሰፈሩት መልዕክት "ለመላው ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ሌት ተቀን በግድቡ ሥራ ላይ ለሚሳተፉ ሁሉ በራሴ እና በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ስም በድጋሜ እንኳን ደስ ያላችሁ" ነው ያሉት።
Nested Portlets
Asset Publisher
መጣጥፎች
— 5 Items per Page