ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የአንድነታችን ማኅተም ነው- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የአንድነታችን ማኅተም ነው- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የአንድነታችን ማኅተም ነው- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የታላቁ የሕዳሴ ግድብ 2ኛ ዙር ውኃ ሙሌት በተሳካ ሁኔታ በመጠናቀቁ የተሰማውን ልባዊ ደስታ ግለጸ::

ምክር ቤቱ ደስታውን በተለያዩ ክፍለ-ዓለማት ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ለወዳጅ ሀገራት እና ግለሰቦች ሁሉ በታላቅ ኩራት እና ሀገራዊ ስሜት በድጋሚ ያበስራል ነው ያለው በመግለጫው፡፡

ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የአንድነታችን ማኅተም፣ የለውጥ ጉዟችን አውታር እንዲሁም የላባችን እና የጥረታችን ማሳያ እንደሆነ ከእኛ አልፎ መላው ዓለም ተረድቶታል፡፡

ይህም በቅርቡ በመንግስታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ባሰማነው የፍትሐዊነት ሐሳብ፤ ዓላማችን በጋራ ሀብት የዕኩል ተጠቃሚነት መርህ መከተል መሆኑን በማያወላዳ አኳኋን ለሚመለከታቸው ሁሉ አስገንዝበናል፡፡

ይህ የጀመርነው የልማት ጉዞ በሁሉም ዘርፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ምክር ቤቱ በአክብሮት ያሳስባል፡፡

በተለይም በአሁኑ ወቅት የውስጥ እና የውጭ ጠላቶቻችን ባለ በሌለ ዓቅማቸው ሀገራችንን ለማፈራረስ እየሠሩ ባሉበት ሁኔታ፤ የእኛ አንድ ሆኖ መቆም ምርጫ የሌለው አማራጭ መሆኑን መረዳት ይኖርብናል ብሏል ምክር ቤቱ፡፡

ይህንንም በጽኑ ዕምነት አጠናክረን የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን በማድረግ ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ ይጠበቅብናል፡፡

በሌላ በኩል፤ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መላውን የሀገራችንን የእስልምና ሐይማኖት ተከታዮች እንኳን ለ1442ኛው ዓመተ-ሒጅራ የዒድ አል-አድሐ ዐረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ሲልም መልዕክቱን እተላልፏል፡፡

በዓሉ በሚገርም ታሪካዊ ግጥምጥሞሽ ከ2ኛው የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ውኃ ሙሌት ጋር መጣጣሙ ደግሞ፤ በዓሉን ልዩ አድርጎታል፡፡

ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ለታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ ያበረከተውን ወደር-የለሽ አስተዋጽዖ፤ ታሪክ መቼም አይረሳውም ነው ያለው ምክር ቤቱ፡፤

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.