ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት መሪነት የሚካሄደው የህዳሴ ግድብ ድርድር በስኬት እንዲቋጭ ቁርጠኛ መሆኗን አስታወቀች - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት መሪነት የሚካሄደው የህዳሴ ግድብ ድርድር በስኬት እንዲቋጭ ቁርጠኛ መሆኗን አስታወቀች

ኢትዮጵያ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ በአፍሪካ ህብረት መሪነት የሚካሄደው ድርድር በስኬት እንዲቋጭ ቁርጠኛ መሆኗን አስታወቀች፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ዙሪያ መግለጫ አውጥቷል፡፡

በመግለጫውም ኢትዮጵያ በህብረቱ አማካኝነት የሚደረገውን ድርድር በስኬት ለመቋጨት የማይናወጥ አቋም እንዳላት አስታውቋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም በህብረቱ አማካኝነት የሚካሄደው የድርድር ሂደት ዋነኛ የመፍትሄ አካል መሆኑንም ገልጿል፡፡

ሂደቱም ሃገራቱ ወደሚፈልጉትና ጠቃሚ በሆኑ ጉዳዮች ላይ መግባባት ላይ እንዲደርሱ ይረዳልም ነው ያለው፡፡

ከዚህ አንጻርም በህብረቱ መሪነት የሚካሄደው ድርድር በስኬት እንዲቋጭና ተቀባይነት ያለው የጋራ ውጤት ይገኝበት ዘንድ ኢትዮጵያ ቁርጠኛ መሆኗንም አስታውቋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር በቀረበው ሀሳብ መሰረት ለመስራት ዝግጁ መሆኗንም ነው የገለጸው፡፡

በተጨማሪም ድርድሩ ውጤታማ እንዲሆን ግብጽና ሱዳን በቅን ልቦና እንዲደራደሩ ኢትዮጵያ ታበረታታለችም ብሏል በመግለጫው፡፡

ሚኒስቴሩ በመግለጫው ሲካሄድ የቆየው ድርድር መቋረጡና ለፖለቲካ ፍጆታ መዋሉ አሳዛኝ መሆኑንም ነው የገለጸው፡፡

ኢትዮጵያ በጉዳዩ ላይ ግልጽ አቋሟን አሳውቃ እያለ ጉዳዩን ወደ ፀጥታው ምክር ቤት መውሰዱ ተገቢነት የሌለውና የማያዋጣ እንደነበርም አስታውሷል፡፡

ከዚህ ባለፈም ጉዳዩ ከምክር ቤቱ ስልጣንና ሃላፊነት ጋር የማይገናኝ እንደሆነ መግለጹን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ኤፍ ሐምሌ 6 2013

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.