‹‹የግብጽና የሱዳን አካሄድ ሁሉም ነገር ለኔ ብቻ ከሚል ስግብግብነት ይመነጫል››ሐጅ አብዱልሃፊዝ ከማልየኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሀብት ማሰባሰብና አጠቃቀም ኃላፊ - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

‹‹የግብጽና የሱዳን አካሄድ ሁሉም ነገር ለኔ ብቻ ከሚል ስግብግብነት ይመነጫል››ሐጅ አብዱልሃፊዝ ከማልየኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሀብት ማሰባሰብና አጠቃቀም ኃላፊ
የግብጽና የሱዳን አካሄድ ሁሉም ነገር ለኔ ብቻ ከሚል ስግብግብነት የሚመነጭ መሆኑን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሀብት ማሰባሰብና አጠቃቀም ኃላፊ ሐጅ አብዱልሃፊዝ ከማል አስታወቁ።
ሐጅ አብዱላሃፊዝ በተለይም ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ ግብፅና ሱዳን በህዳሴው ግድብ ዙሪያ እያራመዱት ያለው እንቅስቃሴ ሁሉም ነገር የኔ ብቻ ይሁን ከሚል ስግብግብነት ይመነጫል፡፡ ሁኔታው ያልተገባና ፍትሐዊነት የጎደለው ነው፡፡
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ ሕዝቦቿን ከጨለማ ለመታደግ እየገነባችው ያለ ግድብ ነው ያሉት ሐጅ አብዱላሃፊዝ ሁለቱ አገሮች እያደረጉት ያለው ያልተገባ እንቅስቃሴ ይህንን ሰብዓዊ ጥረት ለማደናቀፍ እንደሆነ አስታውቀዋል ።
ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ግብጽ ከፍተኛ የሆነ የከርሰ ምድር የውሃ ክምችት ያላትና ከፍተኛ የሆነ ውሃ የምታባክን አገር መሆኗን የጠቆሙት ሐጅ አብዱላሃፊዝ ፤ኢትዮጵያ ውሀ ልታሳጣን ነው በሚል እየሄዱበት ያለው መንገድ ከእውነተኛ ስጋት የመነጨ ሳይሆን የእኛን ማደግ ካለመፈለግና ከምቀኝነት የሚመነጭ ካልሆነ በስተቀር በእነርሱ ላይ ልናደርሰው የምንችለው የከፋ ጉዳት የለም ብለዋል።
ግብጽ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ጎልታ እንድትወጣ አትፈልግም ያሉት ሐጅ አብዱልሃፊዝ፤ የአስተሳሰቡ ምንጭ ኢትዮጵያ ጎልታ ወጣች ማለት እነሱ ያላቸውን የምዕራቡ ዓለም ተሰሚነት ይቀንሳል የሚል ነው ። እያካሄዱ ያለው ዘመቻም ይህንኑ ታሳቢ ያደረገ እንደሆነ አስታውቀዋል።
እንደርሳቸው ማብራሪያ፤ በተለይ በአፍሪካ ቀንድ ኢትዮጵያ ጎልታ ከወጣች የግብጽ ተጽዕኖ የበለጠ እየቀነሰ ይመጣል ብለው ያስባሉ። በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ በመንዛት እየሰሩ የሚገኙትም ተደማጭነታችን ይቀንሳል ከሚል ስጋት ነው።
የአባይ ወንዝ ምንጩ ኢትዮጵያ፣ እየተገነባ ያለው በኢትዮጵያውያን ሃብትና በራሳችን ሉዓላዊ ግዛት ውስጥ ነው ። ስለሆነም በፍትሐዊነት የመጠቀም መብት ከግብጽና ሱዳን ይልቅ የእኛ የላቀ ነው ። ስለዚህ የጋራ ጥቅምን መሰረት በማድረግ መጠቀም እንደምንችል ያለማቅማማት መቀበል እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።
መልማት የሚቻለው አንድነት ሲኖር ነው ያሉት ሐጅ አብዱልሃፊዝ፤ የግብጽና የሱዳን የተቀናጀ የሀሰት ዘመቻ ለመግታት ሁሉም ልዩነቱን ወደ ጎን በመተው በአባይ ጉዳይ ላይ አንድ ሆኖ ሊቆም ይገባል ብለዋል።
ግብጽና ሱዳን በተደጋጋሚ የህዳሴውን ጉዳይ ወደ ጸጥታው ምክር ቤት መውሰዳቸው አግባብም አዋጭም አይደለም ። ምክንያቱም ጉዳዩን መውሰድ ካለባቸውም ወደ አፍሪካ ሕብረት ነበር። ነገር ግን የያዙት ደረቅ ውሸት በመሆኑ ይህን ማድረግ እንዳልደፈሩ አስታውቀዋል ።
በአፍሪካውያን መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶች መፈታት ያለባቸው በአፍሪካውያን ሊሆን ይገባል ። ጉዳዩ መፍትሄ እንዲያገኝ ከፈለጉ የአፍሪካን ጉዳይ በአፍሪካውያን መፈታት አለበት የሚለውን አቋም መቀበል አለባቸው ብለዋል።
አዲስ ዘመን ሐምሌ 5/2013
 
 
 
 

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.