“ግብጽ ለራሷ ስትል ከመጣችበት እኔ ብቻ እየተጠቀምኩ ልቀጥል ከሚለው አስተሳሰቧ ልትወጣ ይገባል” እምሩ ታምራት፤ ዓለም አቀፍ የውሃ ሕጎች ኤክስፐርት - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

“ግብጽ ለራሷ ስትል ከመጣችበት እኔ ብቻ እየተጠቀምኩ ልቀጥል ከሚለው አስተሳሰቧ ልትወጣ ይገባል” እምሩ ታምራት፤ ዓለም አቀፍ የውሃ ሕጎች ኤክስፐርት
አዲስ አበባ፡– ግብጽ ለራሷም ስትል ለዘመናት የቆየችበትን ሁልጊዜ እኔ ብቻ እየተጠቀምኩ ልቀጥል የሚል የተሳሳተ አስተሳሰቧን ካልለወጠች ድርድሩ ወደ አፍሪካ ሕብረት ቢመጣም አሁንም መንገዷን ቀይራ ጫና ለመፍጠር መሞከሯ የማይቀር መሆኑን በዓባይ ወንዝ አጠቃቀም ዙሪያ ከሰላሳ ዓመታት በላይ በአደራዳሪነትና በአማካሪነት የሰሩት ዓለም አቀፍ የውሃ ሕጎች ኤክስፐርት አቶ እምሩ ታም ራት አስታወቁ ።
ሆኖም ኢትዮጵያ እስከ መጨረሻው ድረስ በያዘችው አቋም በመጽናት፤ ለችግሮች ምላሽ በመስጠት ላይ ብቻ ሳይሆን ጥቅሟን የሚያስከበሩላትን ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ሥራዎችን ስትራቴጂ ነድፋ ቀጣይነት ባለው መንገድ ጠንክራ ከሰራች ሊፈጠሩ የሚችሉ ጫናዎችን ሁሉ ተቋቁማ በድርድሩ አሸናፊ ሆና መውጣት እንደምትችል አስታወቁ ።
የጸጥታው ምክር ቤት በታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ያደረገውን ውይይት አስመልክቶ አቶ እምሩ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳመለከቱት ፣ የፀጥታው ምክር ቤት እንዲህ ዓይነት ጉዳዮችን የመመልከት ስልጣን እንደሌለው አስታውቀዋል ።
“ግብጽና ሱዳንም ይህንን ያውቃሉ፤ ሆኖም ጉዳዩን ወደ ፀጥታው ምክር ቤት መውሰድ የፈለጉት በኢትዮጵያ ላይ የተጠናከረ ፖለቲካዊ ጫና ፈጥረው በቅኝ ግዛት ዘመን ያገኙትን የእነርሱን ተገቢና ሚዛናዊ ያልሆነ ጥቅም ለማስቀጠል በማሰብ ነው” ብለዋል።
አገራቱ ጉዳዩን ወደ ፀጥታው ምክር ቤት ሲወስዱት ይህ የመጀመሪያቸው አለመሆኑን፤ የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን ያስታወሱት አቶ እምሩ፤ “ምናልባት ይኸኛውን ትንሽ ለየት የሚያደርገው ግብጽና ሱዳን እነርሱ ብቻ ሳይሆኑ ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ሌሎች አገራትንም አስተባብረው ምክር ቤቱን በመጠቀም በኢትዮጵያ ላይ ይበልጥ ጫና ለመፍጠር መሞከራቸው እንደሆነ አመልክተዋል።
ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች የላይኛው ተፋሰስ አገራት ከዓባይ ወንዝ ውሃ ምንም ዓይነት ውሃ እንዳያገኙ የሚያደርገውን ከቅኝ ገዥዎቻቸው የተረከቡትን ኢ-ፍትሐዊ ስምምነት ኢትዮጵያ በጫና እንድትፈርም የተደረገ ጥረት እንደነበር አመልክተዋል ። ይህ በፍጹም የማይሆን ነገር ነው ። ኢትዮጵያም በውሃዋ የመጠቀም ሉዓላዊ መብት አላት። ጉዳዩን የፀጥታው ምክር ቤት የማየት ስልጣን እንደሌለውም ጠቁመዋል ።
የታችኞቹ ተፋሰስ ሃገራት በተለይም ግብጽ ለራሷም ስትል፣ ለሕዝቧ ጥቅም ስትል ለዘመናት ከቆየችበት ሁልጊዜ እኔ ብቻ እየተጠቀምኩ ልቀጥል የሚል የተሳሳተ አስተሳሰቧን ካልለወጠች በስተቀር ድርድሩ ወደ አፍሪካ ሕብረት ቢመጣም አሁንም ቢሆን መንገዷን ቀይራ ጫና ለመፍጠር መመከሯ የማይቀር መሆኑንም አመልክተዋል።
ኢትዮጵያ ከመጀመሪያው ጀምራ እየተከተለችው ያለው “ማንንም በማይጎዳ መንገድ የዓባይን ውሃ በፍትሐዊነት የመጠቀምና በጋራ የመበልፀግ መርህ” ትክክለኛውና አዋጩ አካሄድ እንደሆነ ያስታወቁት አቶ እምሩ፤ ግብጽ እና ከጎኗ የተሰለፉ ሀገራት የቱንም ያህል ጫና ለማሳደር ቢጥሩ የማይሳካላቸው መሆኑን አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ አሸናፊ እንድትሆን እስከ መጨረሻው ድረስ በያዘችው አቋም መጽናትና ለችግሮች ምላሽ በመስጠት ላይ ብቻ ሳይሆን ጥቅሟን የሚስከበሩላትን ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ሥራዎችን እና ስትራቴጅ ነድፋ ቀጣይነት ባለው መንገድ ጠንክራ መስራት ይጠበቅባታል ብለዋል ።
ለዚህም ድርድሩን የሚመለከቱ ቴክኒካዊ የሆኑ ጉዳዮችን ብቻ ሳይሆን ጥቅሟን በአግባቡ ሊያስጠብቁላት የሚችሉ ዲፕሎማሲያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይም ትኩረት አድርጋ መስራት ይገባታል። በዚህ ረገድ እነርሱ እንደሚያደርጉት ብቻዋን ሳትሆን ቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ስትራቴጅካዊ አጋሮቿን ይዛ ሊሆን እንደሚገባ ጠቁመዋል ።
በተለይም ጉዳዩ ስምንት የሚደርሱ ሌሎች የተፋሰሱ አገሮችን ጥቅም የሚመለከት በመሆኑ እነዚህን አገሮች አስተባብራ ተፅእኖ መፍጠር የሚችል ጠንካራ የዲፕሎማሲና የፖለቲካ ሥራዎችን መስራት አለባት ። ይህንን ማድረግ ከተቻለ ሊፈጠሩ የሚችሉ ጫናዎችን ሁሉ ተቋቁማ በመጨረሻ በድርድሩ አሸናፊ ሆና መውጣት እንደምትችል አስታውቀዋል።
አዲስ ዘመን ሐምሌ 5/2013
 
 
 
 

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.