የፀጥታው ምክር ቤት የህዳሴ ግድብ ጉዳይ የልማት እና አፍሪካዊ ጉዳይ መሆኑን ማረጋገጡ ትልቅ የዲፕሎማሲ ድል ነው-አምባሳደር ዲና ሙፍቲ - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

የፀጥታው ምክር ቤት የህዳሴ ግድብ ጉዳይ የልማት እና አፍሪካዊ ጉዳይ መሆኑን ማረጋገጡ ትልቅ የዲፕሎማሲ ድል ነው-አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የፀጥታው ምክር ቤት የህዳሴ ግድብ ጉዳይ የልማት እና አፍሪካዊ ጉዳይ መሆኑን ማረጋገጡ ትልቅ የዲፕሎማሲ ስኬት መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሰብአዊ እርዳታ ድጋፍ ወደ ትግራይ የሚደረጉ በረራዎች ላይ ጠንካራ ፍተሻና ምርመራ እንደሚደረግም አስታውቋል።
ጉዳዩ ወደ ምክርቤቱ የመለስ እድል እንደሌለው አምባሳደሩ ገልጸው÷ የግብፅና የሱዳን አማራጭ ልማቱን መደገፍ ብቻ ነውም ብለዋል።
የውጭ ገዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ መግለጫ እየሰጡ ነው።
አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በመግለጫቸው ለትግራይ ክልል ለሚደረገው የሰብአዊ እርዳታ የአለም አቀፍ ተቋማት የበረራ ፍቃድ ቢሰጥም፤ እያንዳንዱ በረራ ግን መነሻው ከአዲስ አበባ እንደሆነ ገልፀዋል።
በምክርቤቱ ተለዋጭ እና ቋሚ አባል ሀገራት ጋር በተናጠል የተሰራው የማስረዳት ስራ ፍሬ ማፍራቱን አሳይቷል ብለዋል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በኒውዮርክ ያደረጉት ሰልፍ ተፅእኖ መፍጠር የቻለ እና ኢትዮጵያውያኑ ያላቸውን ሀገር ወዳድነት ያሳዩበት ነው ብለዋል።
አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በመግለጫቸው የተጠናጠል ተኩስ አቁሙ ምክንያት አስመልከቶ ለአምባሳደሮችና ለአለምአቀፍ ተቋማት ተወካዮች ማብራሪያ መሰጠቱን ገልጸዋል።
የግብርና ስራውን ህዝቡ በተረጋጋ መንገድ መከወን እንዲችልና ቡድኑ የደህንነት ስጋት አለመሆኑ ዋና ዋና ምክንያቶች መሆናቸውም መገለጹን ተናግረዋል።
ንፁሃንን ሽፋን በማደረግ ቡድኑ ያደረገሰውን ጥቃት አስመልክቶም መገለጹን ተናግረዋል።
ሰብአዊ ድጋፍ ለማድረግ፣ የበረራ አገልግሎት መፈቀዱን እና አስፈላጊው ፍተሻ መከናወኑ አስገዳጅ መሆኑም መብራራቱን አንስተዋል።
ቡድኑ ለተኩስ አቁሙ ፈቃደኛ አይደለም ይልቁኑ የማይታሰቡ ቅድመ ሁኔታዎችን ማስቀመጡ ማብራሪያ ተሰጥቶበታል ብለዋል።
ሌላው በመግለጫው የተነሳው የናይል ተፋሰስ ሀገራት አምባሳደሮች ጋር የተደረገው ውይይት ነው።
በውይይቱም ግብፅና ሱዳን የግድቡ ጉዳይ ለፀጥታው ምክር ቤት እንዲመራ ማድረጋቸው አግባብ አለመሆኑ ላይ በመግባባት መንፈስ ውይይት ተደርጎበታል ነው ያሉት አምባሳደር ዲና።
ሀገራቱ ለአፍሪካ ህብረት ያላቸውን ንቀት ያሳዩበት መሆኑ መግባባት ላይ መደረሱን ገልፀዋል።
ከዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ አንጻር እስከ ትላንት ድረስ 21 ሺህ 182 ዜጎች በ99 በረራዎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን ተናግረዋል።
ዜጎቹን የመመለሱ ጉዳይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል።
በሀብታሙ ተ/ስላሴ

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.