በዶሃ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለህዳሴ ግድብ የቦንድ ግዢ ፈጸሙ - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

በዶሃ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለህዳሴ ግድብ የቦንድ ግዢ ፈጸሙ

ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በዶሃ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም የዳያስፖራ ማህበራት 25 ሺህ የአሜሪካን ዶላር የቦንድ ግዥ ፈጽመዋል።

በቀጠር የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ማህበር 15 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ዋጋ ያለው የቦንድ ግዥ በያዝነው ሳምንት ፈፅሟል።

የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሳሚያ ዘካሪያ የቦንድ ግዥውን ለፈፀሙ አካላት የቦንድ ሰርተፍኬት ርክክብ ያደረጉ ሲሆን፥ ዜጎች በዚህ ወሳኝ ወቅት ለግድቡ እያሳዩት ያለው ቀጣይነት ያለው ድጋፍ የሚደነቅ መሆኑንም ተናግረዋል።

ሌሎችም ይህንኑ አርዓያነት ያለው ተግባር እንዲደግፉ አምባሳደሯ ጥሪ ማቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኤምባሲው የቦንድ ግዥ በመፈጸም እና በሌሎች ድጋፎች የተሳተፉ ዜጎችን፣ የህዳሴ ግድብ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን አባላት እና የዳያስፖራ አደረጃጀቶችን አመስግኗል።

ኤፍ ሲ፣ ሃምሌ 1/ 2013

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.