በግድቡ ዙሪያ አላስፈላጊ ጫና ለመፍጠር የሚደረገው ጥረት የሚፈለገውን ውጤት ሊያመጣ አይችልም-አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

በግድቡ ዙሪያ አላስፈላጊ ጫና ለመፍጠር የሚደረገው ጥረት የሚፈለገውን ውጤት ሊያመጣ አይችልም-አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ

በሱዳን የኢትዮጵያ ባለሙሉሥልጣን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በሱዳን ለሚገኙ የመገናኛ ብዙኃን የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫቸው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ወንድም ለሆነው የሱዳን ሕዝብ የስጋት ምንጭ ሊሆን እንደማይችል ገልፀዋል፡፡
አምባሳደር ይበልጣል የአባይ ተፋሰስ የኢትዮጵያን ሁለት-ሶስተኛ የውሃ ሀብት የሚሸፍን እንዲሁም የናይልን 86 በመቶ ኢትዮጵያ የምታበረክት ቢሆንም ሀብቱ እያለ እስካሁን ድረስ 65 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን በኤሌክትሪክ እጦት በጨለማ ውስጥ ይኖራሉ ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ እና ሱዳን፣ የጋራ ታሪክ ያላቸው ዕጣፈንታቸውም የተሳሰረ መሆኑን ያስረዱት አምባሳደር ይበልጣል በታሪክ እንደታየው አንዳቸው ለአንዳቸው ጋሻ ሆነው መቆየታቸውን መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለሱዳን ከፍተኛ ጥቅም ያለው በመሆኑም ሱዳናዊያን እና የሱዳን መንግስት ለግድቡ ግንባታ አስፈላጊውን የፖለቲካ፣ የቁሳቁስ የሞራል ድጋፍ ሲያደርጉ እንደቆዩ ጠቅሰዋል፡፡
ከዚህ አኳያ ግድቡ “የሱዳን ኃይል ማመንጫ ግድቦች ከዓመት እስከ ዓመትበሙሉ አቅማቸው ኃይል ለማመንጨት እንደሚረዳ፣ ምርትና ምርታማነትን እንደሚጨመር፣ ወንዙ በበጋ ወቅት ከነበረው ከሁለት እስከ አራት ሜትር ከፍ ስለሚል እና ዓመቱን ሙሉ የተመጠነ ፍሰት ስለሚኖረው ለመጓጓዣነት የተሻለ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር፣ ወደ ሱዳን ግድቦች ይገባ የነበረውን 90 በመቶ ደለል በመቀነስ ሱዳን ለደለል ማስወገጃ በየዓመቱ የምታወጣውን 50 ሚሊየን ዩሮ እንደምታድን፣ ሱዳን በአነስተኛ ዋጋ የኤሌክትሪክ ኃይል ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ማግኘት እንደምትችል፣ የጎርፍ አደጋ ሙሉ በሙሉ በማስወገድ የህይወትና ንብረት ጥፋትን እንደሚታደጋት ገልጸዋል፡፡
ከመረጃ ልውውጥ ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርህ ለማጋራት ዝግጁ ስትሆን የግድቡን ሙሌት በተመለከተ መቼ ምን ያክል ውሃ መያዝ እንዳለበት በሶስቱ ሀገራት ባለሙያዎች መግባባት የተደረሰበት እንደሆነ ጠቅሰዋል።
ጉዳዩ በሶስቱ አገሮች መካከል በሚደረግ ድርድር የሚጠናቀቅ ሆኖ ሳለ፣ በሱዳን እና ግብጽ በኩል ከድንበር ተሻጋሪ ወንዞች አጠቃቅም መርሆዎች ባፈነገጠ መልኩ “የኢትየጵያን የውሃ የመጠቀም መብት ለመገደብ መሻታቸው፣ ቴክኒካዊ የሆነን የግድብ ጉዳይ የጸጥታ እና የፖለቲካ ጉዳይ ለማድረግ ቀን ከሌት እንደሚሰሩ፣ የዐረብ ሊግ አገራትን በማስተባበር በኢትጵያ ላይ ጫና ለማሳደር እንደሚሞክሩ፣ ጉዳዩ ወደ ጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ለመውሰድ ሌት ተቀን በመስራት ጉዳዩን ዓለምአቀፋዊ ለማድረግ እንደሚጥሩ ነገር ግን እንደ ኢትዮጵያ እምነት አላስፈላጊ ጫና ለመፍጠር የሚደረገው ጥረት የሚፈለገውን ውጤት ሊያመጣ እንደማይችል በአጽንኦት ገልጸዋል።
በመሆኑም በአፍሪካ ህብረት ማዕቀፍ ስር በሚደረገው ድርድር ሶስቱን አገሮች ተጠቃሚ የሚያደርግ ስምምነት መድረስ እንደሚቻል የጠቀሱት አምባሳደር ይበልጣል መጀመሪያ የግድቡ አሞላል ዙሪያ ሶስቱ ሀገራት የጋራ መግባባት የደረሱ በመሆኑ በመጀመሪያ ሙሌቱ ዙሪያ መስማማት እና በቀጣይ ድርድሩን በግድቡ ዓመታዊ የውሃ አለቃቅ ዙሪያ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልጸዋል።
ኤፍ ቢ ሲ ፣ ሰኔ 27፣ 2013

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.