የደቡብ ሱዳን ብሔራዊ የምርምር ተቋም የህዳሴ ግድብን በተመለከተ የኢትዮጵያን አቋም እንደሚደግፍ አስታወቀ - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

የደቡብ ሱዳን ብሔራዊ የምርምር ተቋም የህዳሴ ግድብን በተመለከተ የኢትዮጵያን አቋም እንደሚደግፍ አስታወቀ

ኢትዮጵያ በግዛቷ ውስጥ ያለውን የውሃ ሃብት አልምታ የመጠቀም መብት እንዳላት የደቡብ ሱዳን ብሔራዊ የምርምር ተቋም ኃላፊ መናገራቸው ተገለፀ።

ተቋሙ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን በሚመለከት ከግብፅና ሱዳን ጋር በሚደረው ድርድር የኢትዮጵያን አቋም እንደሚደግፍ ግልጽ አድርጓል፡፡

በግድቡ ግንባታና ሙሊት ዙሪያ ኢትዮጵያ ከግብፅና ከሱዳን ጋር ተከታታይ ውይይቶችን ስታደርግ መቆየቷን ሱዳን ፖስት በድረገጹ አስታውቋል።

ኢትዮጵያ ግድቡ በምንም መንገድ በግብፅና በሱዳን የውሃ ፍሰት ላይ ተጽዕኖ እንደማያሳድር ስትወተውት ብትቆይም ሀገራቱ የውሃ ድርሻ ይቀንሳል የሚል ዘመቻ ላይ ናቸውም ብሏል፡፡

ደቡብ ሱዳን ግድቡን ሰበብ ያደረገ ግጭት በሀገራቱ ላይ ብቻ ሳይሆን በቀጠናው ላይም የከፋ ተጽእኖ ስለሚፈጥር ግብጽና ሱዳን ከግጭት በመቆጠብ ጉዳዩን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱት ስትወተውት እንደቆየች ያተተው ዘገባው፤ የህዳሴ ግድብ ውዝግብን በሚመለከት እስካሁን ምንም ዓይነት አቋም አለማንጸባረቋን አሳውቋል።

በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማህዲ የደቡብ ሱዳን ብሔራዊ የምርምር ምኢንስቲትዩት ማኔጂንግ ዳይሬክተር አብርሃም አዎሊችን ሲያነጋግሩ ሁለቱ ሀገራት በጋራ ስለ ሚኖራቸው የትብብር መስኮች እንዲሁም በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ሐሳብ መለዋወጣቸውን ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ መረዳታቸውን ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ለደቡብ ሱዳን ነፃነት ያበረከቱትን አስተዋፅኦ ያስታወሱት ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ፤በሁሉም ችግሮቻችን ጊዜያት ሁሉ ከጎናችን የነበረችው ኢትዮጵያ ከራሷ አልፋ ለምስራቅ አፍሪካም ሆነ ለሌሎች ሀገራት የሚተርፈውን ግድብ የመገንባት ሙሉ መብት አላትማለታቸውን ሱዳን ፖስትን ጠቀሶ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.