የአረንጓዴ ልማትን በማጠናከርና ችግኞችን በመትከል ግድቦች በደለል እንዳይሞሉ ማድርግ ይገባል-ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

የአረንጓዴ ልማትን በማጠናከርና ችግኞችን በመትከል ግድቦች በደለል እንዳይሞሉ ማድርግ ይገባል-ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ

በኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማትን በማጠናከርና ችግኞችን በመትከል ግድቦች በደለል እንዳይሞሉ ማድርግ እንደሚገባ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ገለጹ።

ሚኒስቴሩ ከተጠሪ ተቋማቱ ጋር በለገዳዲ ተፋሰስ አካባቢ የችግኝ ተከላ መርሃ- ግብር ትናንት አካሂዷል።    

የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ፤ ባለፉት ሁለት ዓመታት በሚኒስቴሩና ከተጠሪ ተቋማት 100 ሺህ በላይ ችግኞች መተከላቸውን ገልጸው፤ በኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማትን በማጠናከርና ችግኞችን በመትከል ግድቦች በደለል እንዳይሞሉ ማድርግ ይገባል ብለዋል። 

በአገር አቀፍ ደረጃ 6 ቢሊየን ችግኝ እንዲሁም ለጎረቤት አገራት ደግሞ 1 ቢሊየን ችግኞች መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።

ዝግጅቱ እንዲሳካ ሚኒስቴሩ ከግብርና ሚኒስቴርና ከክልሎች ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን የተናገሩት ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ ህዝቡ በስፋት በመሳተፍ የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።  

የተፋሰስ ልማት ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ግዛው በበኩላቸው፤ ባለሥልጣኑ የአባይ ተፋሰስን ለማልማት በየዓመቱ ችግኞችን የማልማት ተግባራት እያከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል።

በተያዘው የክረምት ወራትም በዓባይ ተፋሰስ አካባቢ የሚተከሉ 74 ሚሊዮን ችግኞች መዘጋጀታቸውን ጠቁመው፤ የውሃ መሠረተ ልማቶችን ደህንነት ለመጠበቅ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል።

ከህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘም ባለፈው ዓመት ከተተከሉት 5 ነጥብ 9 ቢሊየን ችግኞች 1 ነጥብ 6 ቢሊየኑ በአባይ ተፋሰስ ውስጥ መተከላቸውን አስረድተዋል።  

በዘንድሮ ዓመት በአገር አቀፍ ደረጃ ለመትከል ከታቀደው ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ችግኝ በአባይ ተፋሰስ ውስጥ እንደሚተከል አብራርተዋል።  

በዛሬው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ የተሳተፉት አቶ ጎሳዬ ደምሴ፤ ኢትዮጵያን አረንጓዴ ለማድረግ ሁላችንም የድርሻችንን መወጣት አለበን ብለዋል።

በመርሃ-ግብሩ ላይ በስምንት ሄክታር መሬት 10 ሺህ አገር በቀል ችግኞች የተተከሉ ሲሆን የሎሚና አፕል የፍራፍሬ ችግኞችም ተካተውበታል።     

ምንጭ፡- ኢዜአ

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.