”ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የቅኝ ግዛት ዘመን ስምምነቶችን የማስቀጠል ፍላጎት እየታየባቸው ነው‘ – ዶክተር ሰዒድ አህመድ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የውሃ ፖለቲካ ታሪክ ተመራማሪ - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

”ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የቅኝ ግዛት ዘመን ስምምነቶችን የማስቀጠል ፍላጎት እየታየባቸው ነው‘ – ዶክተር ሰዒድ አህመድ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የውሃ ፖለቲካ ታሪክ ተመራማሪ

አሁን ያለውን የዓለም አቀፍ ፖለቲካ አካሄድ የቅኝ ግዛት ስምምነቶችን የማስቀጠል ፍላጎት እየታየበት መሆኑን የውሃ ፖለቲካ አጥኚ ዶክተር ሰዒድ አህመድ አመለከቱ

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህርና የውሃ ፖለቲካ ታሪክ ተመራማሪ ዶክተር ሰዒድ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ የቅኝ ግዛት ዘመን ስምምነቶች ሕግ ሆነው ተግባራዊ እየተደረጉ ነው በማለት የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በዋናነት የአውሮፓ ህብረት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና ሌሎችም የቅኝ ግዛት ዘመን ስምምነቶችን እንዲቀጥሉ ይፈልጋሉ። ይህ ተገቢነት የለውም

ለምሳሌ ብናይ አንድ ሕግ ሁለት ወይም ከዛ በላይ የሆኑ አገራት ከተፈራረሙት በዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ እይታ ለፈራሚ አገሮች ሕግ ነው የተፈራረሙት አገሮች እስካልሻሩት ድረስብለዋል

እነሱ የሚፈልጉት እንደ ዓለም ባንክ አይነት የእነሱን እጀንዳ የሚያራምድ ድርጅት፤ ለምሳሌ የልማት ፕሮጀክቶች ሲቀርቡላቸው እነዚያን የቅኝ ግዛት ዘመን ስምምነቶች ማጣቀሻ በማድረግ እንደ አስገዳጅ ሁኔታ ማስቀመጥ እንደሆነ አመልክተዋል።

እንደ እርሳቸው ገለጻ፤አባይ ላይ ሱዳንና ግብጽ በተለያዩ ጊዜያት የተፈራረሙት ስምምነቶች ለእነሱ ሕግ ናቸው። እነዚህ ሕጎች ሁለት አገሮች በስምምነት ካላፈረሷቸው በስተቀር ተግባራዊ ይደረጋሉብለዋል።

ኢትዮጵያ ስምምነቶቹን አለመፈረሟን ያስታወቁት ዶክተር ሰዒድ፣ ግብጽና ሱዳን የያዙት አቋም ኢትዮጵያ ስምምነቱን እንድትቀበል ነው ተገቢነት እንደሌለው አመልክተዋል።

ፈረንሳይና ሶርያ በተፈራረሙት የጤግረስ ወንዝ ስምምነት ላይ በተመሳሳይ ቱርክ ባልፈረመችው ስምምነት ተገዢ እንድትሆን ይፈልጉ እንደነበር አስታውሰው፤ ቱርክና ኢትዮጵያ ተመሳሳይ የውሃ ፖለቲካ እንደገጠማቸው ጠቁመዋል።

በወቅቱ ቱርክ ግድብ ለመስራት የዓለም ባንክን ስትጠይቅ የሶርያ እና የፈረንሳይ ስምምነት ስላለ እርዳታ እንደማይሰጣት ምላሽ ተሰጥቷት እንደነበረ ያስታወሱት ዶክተር ሰዒድ፤ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እየተከተለ ያለውን አካሄድ ትክክል አይደለም ብለዋል።

‹‹ለኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብም ተመሳሳይ አመለካከት አላቸው የቅኝ ግዛት ዘመን ስምምነቶች የነሱን ፍላጎት ያከበረ እስከሆነ ድረስ ማስቀጠል ይፈልጋሉ›› ያሉት ዶክተር ሰዒድ፤ ኢትዮጵያ ግን ስለማይመለከታት የቅኝ ግዛት ስምምነቶችን እንደማትቀበል አስታውቀዋል።

2015 .. የተፈረመው የመርሆች ስምምነት በሦስቱም አገሮች ርዕሰ ብሔር የተፈረመ ብቸኛው ውል እንደሆነም ገልፀው፤ ውሉ የቅኝ ግዛት ስምምነቶች ያፈረሰ አሁን ያለውን የትብብር ስምምነትን መሠረት ያደረገ እንደሆነ አስታውቀዋል። ግብጾች ይህንን ሕግ በሙሉ ልባቸው ሲቀበሉት አይታይም ብለዋል።

ሱዳንና ግብጽ አሁን እያሳዩት ያለው የጦር ዛቻ ለመተግበር የማይታሰብ መሆኑን በመጠቆምም፤ ሁለቱም አገሮች ጉዳዩን ጦርነት እንደማይፈታው ያውቃሉ ብለዋል። አያደርጉትም እንጂ ካደረጉትም በጦርነቱ ማን ተሸናፊ እንደሚሆን ያውቃሉ፣ ኢትዮጵያም በታሪኳ ጦርነትን የመመከት ችግር እንደሌለባትም አስታውቀዋል።

አዲስ ዘመን ሰኔ 19 ቀን 2013 .

 

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.