የፀጥታው ምክር ቤት ሱዳን እና ግብጽ በአፍሪካ ህብረት መሪነት እየተካሄደ ያለውን ድርድር እንዲያከብሩ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ተጠየቀ - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

የፀጥታው ምክር ቤት ሱዳን እና ግብጽ በአፍሪካ ህብረት መሪነት እየተካሄደ ያለውን ድርድር እንዲያከብሩ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ተጠየቀ

ኢትዮጵያ የፀጥታው ምክር ቤት ሱዳን እና ግብጽ በአፍሪካ ህብረት መሪነት እየተካሄደ ያለውን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር እንዲያከብሩ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጠየቀች፡፡

ኢትዮጵያ ለፀጥታው ምክር ቤት ፕሬዚዳንት በጻፈችው ደብዳቤ ሱዳን እና ግብጽ በህዳሴ ግድብ ድርድር ላይ የፀጥታው ምክር ቤት እንዲገባ ያቀረቡትን ሃሳብ ውድቅ አድርጋለች፡፡

በደብዳቤው የሃገራቱ ድርጊት በህብረቱ መሪነት እየተካሄደ ያለውን ድርድር ያላከበረና በሃገራቱ መካካል ያለውን መተማመን የሸረሸረ መሆኑንም ገልጻለች፡፡

የታችኛው የተፋሰሱ ሃገራት በአፍሪካ ህብረት መሪነት የሚካሄደው ድርድር ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ድርድሩን ዘጠኝ ጊዜ ማቋረጣቸውንም አንስቷል፡፡

ከዚህ ባለፈም የህብረቱን ያላሰለሰ ጥረት አለማክበራቸውን እና ገንቢ ውይይቶችን በተደጋጋሚ መግፋታቸውንም ደብዳቤው ጠቅሷል፡፡

ሁለቱ ሃገራት በግድቡ ውይይቶች ላይ ተገቢ ያልሆኑ ጉዳዮችን ማስገባታቸውን ያነሳው ደብዳቤው፥ አላስፈላጊ በሆነ መልኩ ጉዳዩን የፀጥታና ዓለም አቀፋዊ ይዘት በማላበስ የአፍሪካ ህብረት የሚመራውን ድርድር ለማጨናገፍ መሞከራቸውንም ገልጿል፡፡

ከዚህ ባለፈም የአረብ ሊግን በማስገባት ጉዳዩን የበለጠ ለማወሳሰብ ሞክረዋል ያለው ደብዳቤው፥ የህብረቱን ሚና ባለማክበር በህዳሴ ግድብ ላይ የሚደረገውን ድርድር ለማጓተትና ለማራዘም መሞከራቸውንም ጠቁሟል፡፡

ትብብርን ለማጠናከር የሚደረገው የሶስትዮሽ ድርድርም ሃገራቱ የቅኝ ግዛት ውሎችን፣ ምኞታቸውን እና ፍላጎቶቻቸውን በኢትዮጵያ ላይ ለመጫን የሚያደርጉት ጥረት ማስፈጸሚያ መሆን እንደሌለበትም ገልጿል፡፡

ከዚህ አንጻርም ሱዳን እና ግብጽ ያለ እነሱ እውቅና እና ፍቃድ የህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት እንዳይከናወን የሚከተሉት አካሄድ በዓለም አቀፉ ህግ ያልተደገፈና ያልተተገበረ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥቷል፡፡

የሁለተኛው ዙር የግድቡ የውሃ ሙሌትም የፊታችን ሐምሌ ወር በተያዘለት ጊዜና በሶስትዮሽ ድርድሩ በተደረሰው መግባባት መሰረት ይካሄዳል ማለቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ደብዳቤው የፀጥታው ምክር ቤት ሁለቱ ሃገራት በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት እየተደረገ ያለውን ድርድር አክብረው እንዲንቀሳቀሱ ሃላፊነቱን እንዲወጣም ጠይቋል፡፡

ኤፍ ሲ፣ ሰኔ 18/ 2013

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.