የህዳሴ ግድብ ድርድር የጋራ ተጠቃሚነትን ባከበረ መንገድ እንዲካሄድ የአሜሪካ “ብላክ ኮከስ” አባላት ጠየቁ - መነሻ - am
Nested Portlets
Asset Publisher
Statistics
× አድራሻ: ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስኩየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር
Web Content Search
Asset Publisher
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት በማድረግ ድርድር እንዲካሄድ የአሜሪካ ኮንግረስ “ብላክ ኮከስ” አባላት ጠየቁ።
በግድቡ ጉዳይ ላይ ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ አሁንም የጋራ ተጠቃሚነትን እና ትብብር መሰረት ያረገ ሰላማዊ ድርድር ሊያደርጉ ይገባል ብሏል።
ይህ ድርድር የጋራ ተጠቃሚነትን እና ዓለም አቀፍ ህጎችን ያከበረ ሊሆን ይገባል ነው ያሉት አባላቱ።
ግድቡ በአህጉሩ ትልቁ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ በመሆኑ ኤሌክትሪክ ለጎረቤት ሀጋራት በመላክ መልካም አጋጣሚ ሊሆን እንደሚችልም ጠቁመዋል።
የ“ብላክ ኮከስ” አባላቱ አሜሪካ እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ተዋንያን በፈረንጆቹ 2015 ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ የፈረሙትን የሶስትዮሽ ድርድር ሊያከብሩ ይገባል ብለዋል።
አሜሪካ እና ዓለም አቀፍ ተቋማት የህዳሴ ግድቡን በተመለከተ የአፍሪካ ህብረትን በማማከር ጠቃሚ ሚናውን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል።
ሁሉም ወገኖች ተጠቃሚ የሚሆኑበት ሰላማዊ ድርድር እንዲካሄድ የአፍሪካ ህብረት ወሳኝ ሚና አለውም ነው ያሉት።
የአሜሪካ ኮንግረስ “ብላክ ኮከስ” አባላት የህዳሴው ግድብ ለአህጉሪቱ ካለው ፋይዳ አንጻር እንዲጠናቀቅ ሰላማዊ ድርድርን እንደሚደግፉ አስታውቀዋል።
ኤፍ ቢ ሲ፣ ሰኔ 17 ፣ 2013
Nested Portlets
Asset Publisher
መጣጥፎች
— 5 Items per Page