Asset Publisher

A witness from Egyptian to Digital HIdassie movement on social media

.
ግብፃውያኑ ሙህር ስለ ዲጂታል ህዳሴዎች ዘማች ኢትዮጵያውያን
ለውይይት ያቀረበው ጥናታዊ ፁሁፍ
.

"ኢትዮጵያ በዲጂታል ወታደሮቿ 80⁰/⁰
ፍላጎቷ''ተሳክቶላታል። ከዚህ ሁሉ ስኬት ጀርባ አንድ ጠንካራ ሰው አለ ሲል Sultan Aba Gissaን አድምቆ አስፍሮታል !


እኛ"ግብፃዊያን ተኝተናል ወይም የማይረባ ብሽሽቅ ውስጥ ተዘፍቀን የኢትዮጵያ፣ የዲጂታል ህዳሴ አንቂ ዘማች ወታደሮች ጎል እያስቆጠሩብን ይገኛሉ"

ይሄንን አስተያየት የሰጡት መህር ''አንተር ኤል-አዛብ ይባላሉ፣ ይሄንን መልዕክት ያስታላለፈው በፕሩድ እና በአሌክሳንደሪያ ዩኒቨርሲ የሚማሩ ወጣት ሙህር ግብፃዊያንን በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ለውይይት ባዘጋጀዉ መድረክ ላይ ነው።

"ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድቡን የመጀመሪያ ሙሌት ዕውን ለማድረግ ተናግረው ማሳመን የሚችሉ ዜጎቿን ሁሉ መልምላ እንደ ወታደር አሰልፋብናለች።

ዜጎቹም የተነገራቸውን ነገር መዝግበው የያዙ ያህል አንድ ባንድ ተመሳሳይ መረጃዎችን ደጋግመው ያስተጋባሉ፡፡

ይህ የሚዲያ ሰራዊት ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የመስኖ ሚኒስትር መስሪያ ቤቶች ጋር ተቀናጅቶ የሚዘወር ነው። መሪያቸው ደግሞ ሚስተር አባ ጊሳ የሚባለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመገናኛ ብዙሃን አማካሪው ነው" አለ

በተጨማሪም በመካከላቸው የሚገኙት የአረብኛ ተናጋሪ ዜጎችን አሰማርተው ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በአሰብ ሚዲያዎች በ እየቀረቡ መልእክታቸውን ለሁሉም አረብ ህዝብና ማህበረሰብ በየቀኑ ተደራሽ ሲያደርጉ ነው የሚውሉት። በነሱና በኛ ሙህራን ክርክሮች ላይ እነሱ ነጥብ ጥለው ነው የሚልፉት። በመሀል አስባችሁታል ግን ሲል ቁጭቱን ያብሰለስላል!

የዚህ ዲጂታል ሰራዊት ዓላማ በማህበራዊ መገናኛ አውታሮች አረብኛ ተናጋሪዎች አእምሮ ውስጥ ስለ ዓባይ ያሉ እውነታዎችን በተመለከተ ግራ መጋባት መፍጠር እና ሱዳንና ግብፅን በመነጣጠል ላይ ያተኮረ ዘመቻም ነው። እኛ አገር ግብፁና ሱዳን የተፃፉ ጋዜኞች የቴሌቪዥን ውይይቶ ውሎ ሳያድር በአማርኛ ቋንቋ ተተርጉሞ ለኢትዮጵያውያን ተደራሽ ይደረጋል። እነሱ በቋንቋቸው የሚሉትን ተርጉሞ የሚያቀርብ ግብፃዊ ወይም ሱዳናዊ የለም።

በተቃራኒው እነሱ ግን ኢትዮጵያን በተመከለተ ጥሩም ተባለ መጥፎም ተርጉመው ለሀገራቸው ዜጎች መረጃ እየሰጡ ያነቃሉ። አደረጃጀታቸው እጅግ አስገራሚ ነው፣ አንዱ የቀጥታ ቴሌቪዥን ስርጭት ተሟጋች ቢሆን፣ ያንኛው፣ ክርከሩን በአገራቸው ቋንቋ ተርጉሞ ለወገኖቹ ያቀርባል። በሁሉም መስክ ተናበው ነው የሚሄዱት። በዚህ የተቀናጀ ዘመቻቸው የግብፅንና የሱዳንን ዘማቾች አሸንፈው ከፊት እየመሩ ነው።

በዘመቻው ላይ እንደ ትልቅ ድል ያስገኛለው
ሀገራችን ግብፅ በኢትዮጵያ የቅኝ ገዥ እና የበዝባዥነት እንዲሁም የሴረኝነት ሚና እንዳላት ለአለም በማሳወቅ ነው።


በተቃራኒው እነሱ በግብፅ ላይ በሚደረጉት የሚዲያ ዘመቻ በኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞችና፣ አክቲቪስቶች፣ ፀሀፊዎች የሚተገበር ነው አለ ከዚህ ጀርባ
Selam Esleman የመሳሰሉ መኖራቸውን መዝግቡ

ዋና የኛ አጥቂዎች ደሞ አረብኛ ተናጋሪዎቹ
ናቸው ብሎ ስጋቱን ያሳልጣል። ለነሱ ራስ ምታት ዲጂታል ህዳሴዎች
Musa Sheiko
Mohammed Al-arusi محمد العروسي
Mohamed Tewekel
Nur Tahir
Ustath Jemal Beshir Ahmed
Anwar Ibrahim
Sabrin ዘወተ እንደሚገኙበት መዝግቡ!

ሌላው የእንግሊዝኛ ዘማቾች በአሜሪካ የሚገኙ ሲሆን የንግግር ፕሮግራሙ “የአባይ ነገስታት” በመባል ይታወቃሉ
እነዚህ ዘማቾች የኛ አምባሳደሮችን እግር እግር እየተከታሉ የሚሞገቱ ናቸው ይላል !

ሦስተኛው በስዊድን ውስጥ የኖረ ሲሆን “የኢትዮጵያ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ኢንስቲትዩት” የተባለ ተቋም አቋቁሞ ተግባሩ የኢትዮጵያን የናይል ውሃ ተናጠላዊ መብቷን መጠበቅና ግብፅን በመገናኛ ብዙሃን እየቀረበ የማጥቃት ዘመቻ ላይ ተሰማርቶ የሚገኝ ቡድን ነው አለ.
.
ለነሱ ድል ያስገኛው የኛ ዲጂሎች እንዝላልነት ነው ሲል የግብፅን ዘማቾች ይወቅሳል። ከኢትዮጵያውያን ጋርም ሆኖ
ከሱዳኖች ጋር፣ ስለ ህዳሴ ግድብ ክርክር የሚወጡ ሙህራኖችችን፣ በቴሌቪዥን መስኮት አሳማኝ ውይይት ላይ ከማትኮር ይልቅ ወደስድብና ጩኸት ይገባሉ፣ ክርክሩ የሀሳብ ሆኖ ስድብና ነቆራ ውስጥ መግባት
ለኛ የሽንፈታችን ምልክት ሆኖ ይታያል አለ
የእነሱ ተከራካሪዎች ግን አንድም ስድብ አንድም ጮኸት አያሰሙም ይላል በዚህ ትህትናቸው ነጥብ ይጥሉና ያልፉናል አለ።
.
በነዚህ ድክመቶቻችን በኢትዮጵያ የዲጂታል ህዳሴ ዘማቾች ተበልጠናል ብሎ ሀሳቡን ይቋጫዋል !