Asset Publisher

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ቦንድ ለመግዛት በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን/የዲያስፖራው ህብረተሰብ እንዲያውቀው የቀረበ/ የቦንድ ግዢ ለሚያካሂዱ ዲያስፖራዎች የተዘጋጀ መረጃ

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ቦንድ ለመግዛት በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን/የዲያስፖራው ህብረተሰብ እንዲያውቀው የቀረበ/ የቦንድ ግዢ ለሚያካሂዱ ዲያስፖራዎች የተዘጋጀ መረጃ

 

/ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተዘጋጀ መመሪያ ላይ የተወሰደ/

 

አዘጋጅ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግ/ህ/ተ/አስ/ብ/ም/ቤት ጽ/ቤት የሪሶርስ ሞቢላይዜሽን ዳይሬክቶሬት

 

ሰኔ 2013 ዓ/ም

  • ህዳሴ ግድብ ቦንድ በውጭ ሀገር ገንዘቦች ለሽያጭ የቀረበ
  1. የህዳሴ ቦንድ ባህሪያት
    1. የቦንድ ዓይነት፤-
  • ወለድ የሚከፈልበትቦንድ
  • ወለድ የማይከፈልበት ቦንድ

1.2. የቦንዱ ስያሜ- ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ቦንድ

1.3.  የቦንዱ ባለቤትና አቅራቢ -  ኤሌክትሪክ ኃይል(ኢ.ኤ.ኃ)፣የኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር

1.4. የቦንዱ ወኪል ሻጮች- "የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

1.5. ቦንዱ ለሽያጭ የሚቀርብባቸው ቦታዎች-በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ኤምባሲዎች ወይም ቆንስላዎች ወይም ልዩ መልዕክተኛ ጽህፈት ቤቶች

1.6. ቦንዱ የሚከፈልበት ጊዜ- ቦንዱ የጊዜ ገደብ ሲያበቃ

1.7 ዋስትና - የኢትዮጵያ መንግስት ለቦንዱ ሙሉ ዋስትና ሰጥቶታል

1.8. የገቢ ግብር- ቦንዱ ግዢ የሚገኝ የወለድ ገቢ ከግብር ነጻ ነው

1.9. የባንክ ብድር- ቦንዱን በዋስትና አስይዞ ከሀገር ውስጥ ባንክ ብድር መውሰድ ይቻላል፡፡

2. የቦንድ ዋጋ -

2.1. ዝቅተኛው የቦንድ ዋጋ (minimum bond value)-በዶላር ዩሮ እና ፓውንድ ስተርሊንግ 50 ሆኖ  ባለ 100፣300፣500፣1000፣3000፣5000 እና 10000 የቦንድ ኩፖኖች ለገበያ ቀርበዋል፣

2.2. ከዶላር፣ዩሮ እና ፓውንድ ስተርሊንግ ውጪ ሆነው በሌሎች የውጭ ገንዘቦች በመጠቀም የሚፈጽም ሰው በእለቱ ባለው የውጭ ምንዛሪ ወደ አሜሪካን ዶላር ተቀይሮ ግዢ መፈጸም ይቻላል፡፡ የየዕለቱን የምንዛሪ ምጣኔ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድረ-ገፅ መመልከት ይቻላል፡፡

3. የቦንድ የክፍያ ጊዜ (maturity period )

3.1. የቦንዱ ዝቅተኛ የክፍያ ጊዜ 5 ዓመት ሲሆን ከፍተኛው ደግሞ 10 ዓመት ነው፡፡

4. ቦንድ ለመግዛት መሟላት የሚገባቸው ሁኔታዎች

4.1. ቦንዱ የሚሸጠው ለኢትዮጵያዊ/ት ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ/ት ብቻ ቢሆንም የአባይ ተፋሰስ አገሮች ቦንዱን ለመግዛት ፍላጎት ካላቸው መግዛት እንዲችሉ የተፈቀደ ነው

4.2. ትውልደ ኢትዮጵያ የውጭ አገር ዜጎች የተወላጅነት መታወቂያ ባይኖራቸውም ኤምባሲው/ቆንሲላ ጽ/ቤቱ ትውልደ ኢትዮጵያ መሆናቸውን በራሱ መንገድ እስካረጋገጠ ድረስ የቦንድ ግዢ መፈፀም ይችላሉ፣

4.3. ፓስፖርት ይሁን የኮሚኒቲ መታወቂያ ካርድ ያልያዙ ዜጎች በሚያጋጥሙበት ጊዜ ሚሲዮኑ በራሱ መንገድ ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን እስካረጋገጠ ድረስ የቦንድ ሽያጭ ፎርሙ ላይ የገዢው ፎቶግራፍ  የሚያያዝ በመሆኑ መታወቂያ ካርዱ ባይኖራቸውም የቦንድ ግዢ መፈጸም ይችላሉ፡፡

4.4. ሀገር ውስጥ በተከፈተ የውጭ ምንዛሪ ሂሳባቸው ላይ የቦንድ ግዢ መፈጸም የሚፈልጉ ተወላጆች ከሂሳባቸው ወጪ በማደረግ ቦንድ መግዛት ይችላሉ፡፡

5. የቦንድ ወለድ -

5.1. ወለድ መታሰብ የሚጀምርበት ጊዜ፡- የቦንድ ወለድ መታሰብ የሚጀምረው ቦንዱ ከተገዛበት ወይም የቦንድ ግዢ ከተፈጸመበት ቀን ጀምሮ ይሆናል፣

5.2.የወለድ ምጣኔው በየ6ወር የሚለዋወጥ ሲሆን በየጊዜው ያለውን የወለድ ምጣኔ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድረ-ገጽላይ ማግኘት የሚቻል ሲሆን በተጨማሪም በውጭ ጉዳይ ሚ/ር በኩል ለኤምባሲዎች ሚላክ ይሆናል፣

5.3. የወለድ አጠቃቀም- የወለድ ክፍያ የሚፈጸመው የቦንዱ ግዢ የተፈጸመበትን የምንዛሪ አይነት መነሻ በማደረግ በዶላር ፣ፓውንድስተርሊንግ እና ዩሮ ሲሆን ገዢው ወለዱን፤-

  • በግንባር በመቅረብ ወይም በህጋዊ ወኪል በኩል መውሰድ፣
  • ለሌላ ተጨማሪ ቦንድ ግዢ ማዋል፤
  • በውጭ ምንዛሪወይም በብር በሚከፍተው ሒሳብ ገቢ ሊያደርግ፣
  • ለተለያዩ ክፍያዎች ሊጠቀምበት ይችላል፡፡

6. ቦንዱን ለመግዛት አማራጭ መንገዶች

6.1. የክፍያውን ገንዘብ በስዊፍት/ swift/ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማስተላለፍ-በኢትዮጵያ ንገድ ባንክ correspondent banks በኩል -ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ swift ግንኙነት ካላቸው 40 ታላላቅ ባንኮች በኩል መላክ ይቻላል፣

  • የባንኮቹ ዝርዝር ከኤምባሲዎች ቆንሲላ ጽ/ቤቶች ልዩ መልዕክተኛ ጽ/ቤቶች እና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድረ-ገፅ (WWW.combanketh.com) ማግኘት ይቻላል፣
  • ቦንድ ገዢው በቅድሚያ የቦንድ ገዢ ቅፅ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድረ-ገጽ በመውሰድ ይሞላና ወደ አቅራቢያው ባንክ በመሄድ ገንዘቡን በswift በሚከተለው አድራሻ መላክ ይጠበቅበታል፣
  • እነዚህን correspondent banks በመጠቀም በዶላር ወይም በዩሮ ወይም ፓውንድ ስተርሊንግ 500 እና ከዚያ በላይ የሆነ የቦንድ ግዥ የሚፈጽም ከሆነ የመላኪያ ገንዘቡ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የሚሸፈን ይሆናል፤

Step 1. የዶላር አካውንት አድራሻ፤-

  • Commercial Bank of Ethiopia churchil Avenue
  • Trade Service
  • Foreign Transfer NR/NT Account
  • Account No. 0270255774200
  • SWIFT Code: CBETETAA

የዩሮ አካውንት አድራሻ፤-

  • Commercial Bank of Ethiopia churchil Avenue
  • Trade Service
  • Foreign Transfer NR/NT Account
  • Account No. 2070255950700
  • SWIFT Code: CBETETAA

የፓውንድ ስተርሊንግ አካውንት አድራሻ፤-

  • Commercial Bank of Ethiopia churchil Avenue
  • Trade Service
  • Foreign Transfer NR/NT Account
  • Account No. 0470255944000
  • SWIFT Code: CBETETAA

Step 2. ገዥው የሞላውን ቅፅ ፣ ገንዘቡን የላከበትን ደረሰኝ ኮፒ ከፓስፖርት ኮፒ ወይም የኮሚኒቲ መታወቂያ ወይም የተወላጅነት ማረጋገጫ መታወቂያ ኮፒ ጋር አያይዞ ከሚከተሉት አማራጮች ውስጥ በመጠቀም ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይልካል፣

  • በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የe-mailአድራሻ፤- (hidasebond@combanketh.com)
  • በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፓ.ሣ.ቁ.225 አዲስ አበባ፣
  • በአቅራቢያው በሚገኝ ኤምባሲ ወይም ቆንስላ ጽ/ቤት ወይም ልዩ መልእክተኛ ጽ/ቤት፣
  • በግለሰብ በኩል መላክ ይቻላል፡፡

Step 3. የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መረጃው እንደደረሰው ገንዘቡ በትክክል ገቢ መደረጉን በማረጋገጥ ገዢው በመረጠው አድራሻ ቦንዱ እንዲደርሰው ያደርጋል፡፡ገንዘቡ ስለመድረሱም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለገዢው በኢሜል አድራሻው ማረጋገጫ ይልክለታል፣

6.2. correspondent ሂሳብ በሌለባቸው ባንኮች- /Bank having Bilateral key with CBE/ በኩል-  የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ correspondent ሂሳብ ካለተከፈተባቸው 384 ባንኮች ጋር የ SWIFT ግንኙነት አለው፣

  • የባንኮቹ ዝርዝር ከኤምባሲዎች ቆንሲላ ጽ/ቤቶች ልዩ መልዕክተኛ ጽ/ቤቶች እና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድረ-ገፅ (WWW.combanketh.com) ማግኘት ይቻላል፣
  • correspondent ሂሳብ በሌለባቸው ባንኮች ተጠቅሞ ገዢው በዶላር ወይም ዩሮ ወይም ፓውንድ ስተርሊንግ 1000 እና በላይ ክፍያ የሚፈጸም ከሆነ የመላኪያ ወጪ ሙሉ በሙሉ በኢ.ኤ.ኃ የሚሸፈንለት ይሆናል፣

6.3. የክፍያውን ገንዘብ በኤምባሲ /ቆንሲላ ጽ/ቤት/ ልዩ መልዕክተኛ ጽ/ቤት በኩል ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማስተላለፍ፤-

  • ማንኛውም ሰው በአቅራቢያው በሚገኝ ኤምባሲ ወይም ቆንሲላ ወይም ልዩ መልእክተኛ ጽ/ቤት በመቅረብ ግዢ መፈጸም ይችላል፣
  • ኤምባሲ ወይም ቆንሲላ ወይም ልዩ መልእክተኛ ጽ/ቤት ተሄዶ ለሚፈጸም ማንኛውም የቦንድ ግዢ የመላኪያ ክፍያ አይጠየቅም፣
  • ኤምባሲው ከቦንድ ሽያጭ የተሰበሰቡ ገንዘቦችን ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲያስተላልፍ የመላኪያ ወጪውን ከተላከው ገንዘብ ላይ ተቀናሽ እንዲሆን በማስደረግ እንዲሸፈን ያደርጋል፡፡
  • ገዢው ክፍያውን በኤምባሲ ወይም በቆንስላወይም ልዩ መልዕክተኞች ጽ/ቤት ሲፈጸም ወዲያውኑ የቦንድ ኩፖን በኤምባሲ ወይም በቆንስላወይም ልዩ መልዕክተኞች ጽ/ቤት ያገኛል፡፡

6.4. የክፍያውን ገንዘብ በገንዘብ አስተላላፊ ኤጀንት /Money Transefer Agent / ወደ ኢትየጵያ ንግድ ባንክ ማስተላለፍ፤-

  • በመካከለኛው ምስራቅና በለንደን የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ በሰንጠረዥ ላይ የተዘረዘሩ የሃዋላ ድርጅቶችን በመጠቀም የቦንድ ግዥ መፈጸም ይችላሉ፣
  • ገዥው በቅድሚያ የቦንድ ግዥ ቅፅ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድረ-ገፅ በመውሰድ ይሞላና ፓስፖርት ወይም የመኖሪ ፈቃድ ይዞ የሃዋላ ድርጅቶቹ ጋር በመቅረብ ገንዘቡን በሚከተለው አድራሻ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማስተላለፍ ይችላል፣
  • ክፍያውን ለማስተላለፍ የመላኪያ ወጪ ሙሉ በሙሉ በኢ.ኤ.ኃ የሚሸፈን ይሆናል፣

Step 1. የዶላር አካውንት አድራሻ፤-

  • Commercial Bank of Ethiopia churchil Avenue
  • Trade Service
  • Foreign Transfer NR/NT Account
  • Account No. 0270255774200
  • SWIFT Code: CBETETAA

የዩሮ አካውንት አድራሻ፤-

  • Commercial Bank of Ethiopia churchil Avenue
  • Trade Service
  • Foreign Transfer NR/NT Account
  • Account No. 2070255950700
  • SWIFT Code: CBETETAA

የፓውንድ ስተርሊንግ አካውንት አድራሻ፤-

  • Commercial Bank of Ethiopia churchil Avenue
  • Trade Service
  • Foreign Transfer NR/NT Account
  • Account No. 0470255944000
  • SWIFT Code: CBETETAA

ሰንጠረዥ ፤- የሃዋላ ድርጅቶች ዝርዝር ከነአድራሻቸውና የሚሰሩባቸው ሃገራት

ተ.ቁ

የሃዋላ ድርጅቱ ስም

አድራሻ

የሚሰሩባቸው አገሮች

1

ላሪ ኤክስቼንጅ

Tel +97126223225

Fax +97126223220

P.o.Box 988 Abudhabi, UAE

ዱባይ፣አቡዳቢ

2

ስፒድ ሬሚት

Tel +96614774770

Fax +966500584993

Samba Financial Group,

P.o.Box 833Riyad,11421

Kindgom of Saudi Arabia

ጅዳ፣ሪያድ እና አካባቢው

3

ዘንጅ ኤክስቼንጅ

Tel +97317253171

Fax +97317214405

 

ባህሬን

4

አላሙዲ ኤክስቼንጅ

Tel +6474515

Fax +6477733

P.o.Box 123 Jeddah 21411

ጅዳ

5

ብሉ ናይል አፍሪካን አርት

Tel (+442)7956162303

Fax +4422076222244

300 Clapharm Road

London SW99 AE

London

UK

ለንደን

6

ኤክስፕረስ የሃዋላ አገልግሎት

Tel +97126521367

Fax +97126355890

P.o.Box 170 Abudhabi, UAE

ዱባይና ኩዌት

 

6.5. በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ ባንኮች ውስጥ ከሚገኘው የውጭ ምንዛሪ ሒሳባቸው ክፍያውን መፈጸም፤-

  • ይህ የባንክ ሂሳብ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሀገር ውስጥ የሚከፍቱት የውጭ ምንዛሪ ሒሳብ ነው፣
  • ግዥው ከውጭ ምንዛሪ ሒሳብ ላይ ተቀናሽ ተደርጎ የሚከፈል ከሆነ ገዥው ከሂሳቡ እንዲቀነስ መስማማቱን የሚገልጽ የተፈረመ የክፍያ ትእዛዝ በደብዳቤ ወይም በቼኩ ለባንኩ መላክ ይኖርበታል፣
  • ከግለሰቡ የውጭ ምንዛሪ ሂሳብ ክፍያው ከተፈጸመ በኃላ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቦንዱን ለገዥው በመረጠው አድራሻ እንዲደርሰው ያደርጋል፡፡

7. የዲያስፖራ የስጦታ አካውንት

7.1.  የዲስፖራ ስጦታ አካውንት በተመለከተ መረጃ በተመለከተ -ማንኛውም በውጭ አገር የሚኖር ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ስጦታ ለማድረግ የሚፈልጉ  ከዚህ በሚከተለው የስጦታ አካውንት ገቢ እንዲያደርጉ እንገልጻለን፤-

የከረንሲው አይነት

የታላቁ ሀዳሴ ግድብ ግንባታ የስጦታ ሂሳብ ቁጥር

USD

0270256128600

EURO

2070256128600

GBP

0470256128600