Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

About Us

ከዋናው ግድብ RCC Dam ግርጌ ከአባይ ወንዝ በቀኝና በግራ በኩል ሁለት የኃይል ማመንጫ ቤቶች ግንባታ ስራ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡ ሁለቱ የኃይል ማመንጫ ቤቶች አስራ ሦስት ዩኒቶች እንዲኖሩት ተደርጎ እየተገነባ ነው፡፡ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በዓመት በአማካኝ 15,759 ጊጋ ዋት ሰዓት ኢነርጂ የማመንጨት አቅም እንዲኖረው ታቅዶ እየተገነባ ያለ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ነው፡፡

ቀደም ብለው ኃይል በሚያመነጩት ዩኒቶች (በዩኒት 9 እና 10)፤ እንዲሁም በሌሎቹ በቀኝም በግራም ባሉ ዩኒቶች የኤሌክትሮ ሜካኒካል እና ኃይድሮ ሜካኒካል ተከላ እና የአርማታ ሙሌት ሥራዎችም በቅንጅት እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡

የግድቡ አጠቃላይ ገጽታ

የወንዙን አቅጣጫ ለማስቀየር የተከናወኑ ሥራዎች

የአባይ ወንዝ በአራተ ዳይቨርሽን ቦክስ ከልቨርቶች ከደሮው አቅጣጫ በማስቀየስ እንዲፍስ እየተደረገ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ሁለቱ ተዘግተው በቀሪዎቹ እየፈሰሰ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ወቅት የዳይቨርሽን ከልቨርት የላይኛውና የታችኛው በሮች ያለ ችግር መዘጋትና መከፈት የሚያችሉ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል፡፡

ውሃ ማስተንፈሻ በሮች (Spillways)

  • ፕሮጀክቱ የሚፈጠረው ሰው ሰራሽ ሃይቅ (Reservoir)  የማጠራቀም ከፍታከባህር ጠለል በላይ እስከ 640 (Full Supply Level) የሚደርስ ይሆናል፡፡ የውሃው መጠን ከ640 . ከባህር ጠለል በላይ ቢጨምር፤ ጭማሪውን የውሃ መጠን በቀላሉ ማስተንፍስ የሚያስችሉ ሶስት በሮች /Spill ways/ ያሉ ሲሆን፤ እነኝህም በሮች የሚኖረውን ተጨማሪ የውሃ መጠን (ሙላት) ተቀብለው ከግድቡ በታች ለመልቀቅ የሚያስችሉ ናቸው፡፡

እነኝህም ከዋናው ግድብ ግራ በኩል መዝጊያ ያለው የውሃ ማስተንፈሻ (Gated Spillway)፤በዋናው ግድ ብመካከለኛ ክፍል (Ungated spillway) እና በሳድል ግድቡ በስተቀኝ በኩል የሚገኝ ውሃ ማስተንፈሻ (Emergency Spillway) የሚገኙ ሲሆን ግንባታቸውም በመጠናቀቅ ላይ  ይገኛል፡፡

የኮርቻ ግድብ (Saddle Dam)

ኮረቻ ግድቡ አይነት ከራስጌ በኩል ባርማታ የተለበጠ ድንጋይ ሙሌት ሲሆን የሙሌት መጠ 15 ሚሊዮን ኪዩቢ ክሜትር፤ ከፍታ50 ሜትር ና ርዝመ5.2 ኪሎ ሜትር የግባታ ስራው ተጠናል፡፡

ፕሮጀክቱ ከተጀመረ እስከ ዛሬ ድረስ ያለው የሥራ አፈፃፀም በተመለከተ የሲቪል ሥራ 86.33% ተጠናቋል፤ የግድቡ ዳርና ዳር የመጨረሻው ከፍታ ከበሃር ወለል በላይ 645 ሜትር ላይ ደርሷል:: በግድቡ ውስጥ መተከል የነበረባቸው የውሀ ማስተላለፊያ የብረታ ብረት ሥራዎች ባለመጠናቀቃቸው መካከለኛዉ አካል ወደ ሚፈለገው ከፍታ ሊደስ አልቻለም፡፡ የኤሌክትሮ መካኒካል ሥራዎችን በተመለከተም 42.26 % እንዲሁም የብረታ ብረት ሥራው የሚታረሙት ሥራዎች ታርመውና ተስተካክለው 20.37%  ተከናውነዋል፡፡ ይህም አጠቃላይ የፕሮጀክቱ ፊዚካል አፈፃፀም 71.59%አድርሶታል፡፡

ሀይቁ የሚተኛበት የምንጣሮ ስራ 30% ገደማ የተከናወነ ሲሆን የመልሶ ማቋቋምና ግንባታ ሥራም 72 % ላይ ደርሷል፡፡

እስከዛሬ ድረስ እነዚህን ሥራዎች አካቶ በአጠቃላይ ለፕሮጀክቱ የተፈፀመው ክፍያ ወደ 99 ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡ኮንትራቱ መጀመሪያ በአንድ ኮንትራክተር ይሰራል ተብሎ ታህሳስ 2003 ዓ.ም የተፈረመ ሲሆን መንግሥት ኮንትራቱ በሁለት የሲቪልና ፕላንት ኮንትራቶች እንዲከፈልና የፕላንት (የጀነሬተር፣ ተርባይን እና የውሀ ማስተላለፊያና የመቆጣጠሪያ በሮች የብረታ ብረት ሥራዎችን) የብረታ ብረታ እና ኢንጂነሪን ኮርፖሬሽን እንዲሰራው ተወስኖ ህዳር 2004 ዓ.ም ከብረታ ብረታ እና ኢንጂነሪን ኮርፖሬሽን ጋር ኮንትራት ተፈርሟል፡፡

በግንባታ ወቅት ጥልቀት ያለዉ የልል ድንጋይ ሸለቆ በማጋጠሙ የውሀ ጠለፋውን እና የግድብ የመሠረት ሥራው ዘግይቷል፡፡ ከዚህ ጋር የተያያዘ ማንኛዉም ተጨማሪ ወጪ በተገባዉ ዉል መሠረት በኮንትራክተሩ ተሸፍኗል፡፡ ይህም የፕሮጀክቱ ኃይል የማመንጨት ጊዜ በሶስት አመት አዘግይቶታል፡፡ በ2009ዓ.ም የመጀመሪያው ሁለት ዩኒቶች ኃይል ማመንጨት ይጀምራሉ ተብሎ የታቀደበት ጊዜ ቢሆንም ይህንኑ ከፍጻሜ ለማድረስ በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የሚሰሩ ሥራዎች በመዘግየታቸዉና ኮርፖሬሽኑ የገባውን የሥራ ግዴታ በተያዘለት ጊዜ ባለመፈፀሙ እንደገና ተጨማሪ የፕሮጀክት የጊዜ መንሸራተት አጋጥሞአል፡፡ ሌላዉ ግምት ዉስጥ መግባት ያለበት እንደዚህ ዓይነት ግዙፍ ሜጋ ፕሮጀክት በአራት ዓመት ውስጥ ኃይል ያመነጫል ብሎ ማሰብ ትክክለኛ ግምትና እቅድ አልነበረም፡፡

ይህ ፕሮጀክት በፋስት ትራክ የግንባታ ሂደት እንዲሰራ በመታሰቡ ዝርዝር የዲዛይንና ምርመራ የቅድመ ኮንስትራክሸን ሥራዎች ከግንባታው ሥራ ጎን ለጎን እንዲከናወኑ መታቀዱና የፕሮጀክቱ የጊዜ ሰሌዳም በዚህ ላይ በመመስረቱ ያልታሰቡ የከርሰምድር ችግሮች በማጋጠማቸው የጊዜ መንሸራተት አጋጥሟል፡፡

በአሁኑ ወቅት የፕሮጀክቱን ወሳኝ ሥራዎች በመለየት ፕሮጀክቱን ወደ ትራክ ለመመለስ ከግድቡ ጋር የሚገናኙ ወሳኝ የብረታ ብረት ሥራዎች እና ከማመንጨት ጋር የተገናኙ ሥራዎች ተለየተዉ አስፈላጊዉ የእርምት እርምጃ ተወስዶ የፕሮጀክቱ ግንባታ እንዲፋጠን እየተደረገ ነዉ፡፡ እነዚህም ሥራዎች የግድብ ውሀ ማስተንፈሻ (Bottom Outlet) ሥራ፣ የወንዝ አቅጣጫ ማስቀየሪያ (Culvert) በሮች እንዲከፈቱና እንዲዘጉ የማድረግ  ስራዎች፣ ለተርባይኖች የውሃ ማስተላለፊያ አሸንዳዎችና የመቆጣጠሪያ በሮች ግንባታ እና የግድቡን ሥራ በማጠናቀቅ ተርባይንና ጀነሬተሮችን ተክሎ ኃይል ማመንጨትና የፕሮጀክቱን ግንባታ ማጠናቀቅ ናቸው፡፡

በነበረዉ የፕሮጀክት አመራርና አካሄድ ፕሮጀክቱ ተጠናቆ መንግሥትና ሕዝብ የሚጠብቀውን ዉጤት ማስገኘት እንደማይቻል በተደጋገሚ የፕሮጀክቱ ባለድርሻ አካላት አመራሮች ባካሄዷቸው ስብሰባዎች ድምዳሜ ላይ በመደረሱ ከብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖርሬይሽን ጋር የተገባዉ ኮንትራት ተቋርጦ ከሌሎች ዓለምአቀፍ ተቋራጮች ጋር አዳዲስ ስምምነቶች እንዲሁም ከብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሸን ጋር የንዑስ ተቋራጭነት ስምምነት ከነበራቸው ጋር የኮንትራት ማሻሻያዎች ተደርገዋል::ቀደም ሲል በውል ላልታሰሩትም ሥራዎች ከፕሮጀክቱ ጋር ግንኙነት ላላቸዉና በተመሳሳይ ሥራ በሀገር ዉስጥ እየሰሩ ያሉ ተቋራጮች ተለይተው በውስን ጨረታ ግዥ እንዲካሄድ ተወስኖ በዚሁ አግባብ ስምምነት ተፈፅሟል፡፡፡

በዚህም ከብረታ ብረት እና ኢንጂነሪግ ኮርፖሬሸን ጋር የነበሩት ውሎች ተቋርጠዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ቀድሞ ብረታ ብረት እና ኢንጂነሪግ ኮርፖሬሸን እንደንዑስ ኮንትራክተሮች ይዞ ያሰራቸው የነበሩትን ኮንትራክተሮች ሙሉ ኃላፊነት ወስደው እንዲሰሩ የኮንትራት ማሻሻያ በማድረግ ወደሥራ ተገብቷል:: ቀደም ሲል ውል ያልተፈረሙላቸው ሥራዎችም በውስን ጨረታ የግዥ ሂደት ተጠናቀው ሰባት ኮንትራቶች ተፈርመውየብረታብረትና ኤሌክትሮ መካኒካልሥራዎች የፋብሪካና ገጠማ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

እንደዚህ ዓይነት ግዙፍና ውስብስብ ፕሮጀክት በሥራው ልምድ የሌለው ኩባንያ ቀርቶ ለዘመናት ልምድ ላካበቱ ኩባንያዎችም አብዛኛዎቹ በተባለው ጊዜ ለመፈፀም ከፍተኛ ፈተና ይሆንባቸዋል፡፡ እንደህዳሴ ፕሮጀክት ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ልምድ ባካበቱ የሥራ ተቋራጮች እንኳን ተሰርተው ከአስር ፕሮጀክቶች ስምንቱ በተባለዉ ጊዜ አይጠናቀቁም፡፡ በሌላ በኩል እንደዚህ ዓይነት ዉሳኔዎች በትክክል ከተመሩና ከሌሎች ሀገሮች ልምድ ጋር ከተቀመሩ የሀገርን አቅም ለመገንባት ከፍተኛ ጠቀሜታ አላቸዉ፡፡

የልምድ ማነስ፣ ለመማር ዝግጁነት ያለመኖር፣ የፕሮጀክት አስተዳደር ልምድ ውስንነት፣ የፕሮጀክቱን ጥልቀትና ውስብስብነት በትክክል ተረድቶ አፋጣኝ የመፍትሄ እርምጃ በወቅቱ ያለመውሰድ እና ሥራዎችን በጊዜ ሰሌዳ አስቀምጦ ወሳኝ የሆኑትን በመለየት አስፈላጊ ትኩረት አለመስጠት በፕሮጀክቱ የግንባታ ሂደት ላይ የታዩ ዋና ዋና ችግሮች ሲሆኑ የተሰሩትን ሥራዎች አስመልክቶ በተለይም ከፍተኛ የጥራት ጉድለትና የጊዜ ሰሌዳ መጓተት ተስተዉሏል፡፡ የተገዙትም የኃይል ማመንጫ ጀነሬተሮችና ተርባይኖች ከነተጓዳኝ ዕቃዎቻቸው በየቦታውና በየወደቦች ጭምር ተበታትነው የሚገኙ በመሆናቸው ተጨማሪ ወጪን አስከትለው ነበር፡፡

የትኩረት አቅጣጫን በተመለከተ ቀድመው ኃይል ያመነጫሉ ተብለው በፕሮጀክቱ  የታሰቡት ዩኒቶች ግድቡ ሳይጠናቀቅ በዝቅተኛ የግድብ ከፍታ 60 ሜትር (የውሃው ሙሌት ከባህር ወለል በላይ 560 ሜትር ሲድርስ ) ሁለት ዪኒቶችን በመጠቀም ኃይል ለማመንጨት የሚያስፈልጉ የውሃ ማስተላለፊያ የብረት አሸንዳዎች ከመቆጣጠሪያ በሮችጭምር፣ ሁለት ተርባይንና የጀነሬተሮች ተከላ የግድቡ የውሃ ማስተንፈሻ (Bottom Outlet)፣ የወንዝ አቅጣጫ ማስቀየሪያ ቱቦ በሮች እና ከሌሎች የኃይል ማመንጫና ማስተላለፊያ እንዲሁም ተጓዳኝ ሥራዎችበማጠናቀቅ በቀጣይ በ 2013 የሶስተናው ሩብ ዓምት ገድማ በሁለቱዪኒቶች ኃይል ማመንጨት መጀመርና አጠቃላይ የግንባታውን ሥራ በ2015 ዓ.ም ማጠናቀቅ ነው::

በዓለም ላይ እንደዚህ ዓይነት ግዙፍና የውሀ ሙሊታቸው ረዘም ያለ ጊዜ የሚወስዱ ግድቦች ሁሉም ተርባይንና ጀነሬተሮች ተከላ በአንድ ጊዜ ሳይሆን ደረጃ በደረጃ መሰራታቸው የተለመደ ነው፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ከወጪ አንፃር አዋጭነት የሌላቸውና ለግንባታው የፈሰሰባቸው ከፍተኛ ገንዘብም ታስሮ የተቀመጠ ኢንቨስትመት ይሆናል፡፡ስለዚህም የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትም በመጀመሪያ ቀድመው ኃይል የሚያመነጩ ሁለት ዩኒቶች በመቀጠልም ቀሪዎቹ አስራ አንዱ ዩኒቶች ተራ በተራ የስራውን ሂደትና የውሃውን ሙሌት ታሳቢ በማድረግ ኃይልየሚያመነጩ ይሆናል፡፡

የፕሮጀክቶች የወጪ ንረትና በተያዘላቸዉ ጊዜ አለመጠናቀቅ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ላይ ብቻ የደረሰ ሳይሆን የችግሮቹ ምንጭና መጠን ይለያይ እንጂ በሁሉም የዓለማችን ክፍል የሚከሰት ነው፡፡ ዋናዉ ትኩረታችን ሊሆን የሚገባው ከችግሮቹ እንዴት እንወጣ የሚለው በመሆኑ ለተከሰቱት ችግሮች ተገቢ የሆነ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ተለይተው የመፍትሄ አቅጣጫዎች ተቀምጦላቸዋል፡፡ ለኤሌክትሮ ሜካኒካልና የሃይድሮሊክ እስቲል እስትራክቸር ስራዎች አዳዲስ ኮንትራቶች ተፈርመው የዲዛይን፣ የፍብረካ፣ የአቅርቦትና የተከላ ሥራዎችም በመከናወን ላይ ናቸው

ታላቁ የህዳሴ ግድብ የኔ፣ የኛ የ110 ሚሊዮን ጀግኖች ኢትዮጵውያን ግድብ ነው!

 

Pages: 1  2