ስለ ግድቡ - am
Statistics
About Us
የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፋይዳዎች
ኘሮጀክቱ ሲጠናቀቅ በዓመት በአማካይ 15,759 ጊጋዋት ሰዓት ኢነርጂ በማመንጨት ለሃገር አቀፍ የኤሌክትሪክ ትስስር ሥርዓት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፤ ኤሌክትሪክ ያልተዳረሰባቸው የገጠር መንደሮችና ከተሞች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግና አቅርቦቱን አሁን ካለበት 44 በመቶ ወደ 90 በመቶ ከፍ ለማድረግ የተያዘውን ግብ ለማሳካት የዚህ ኘሮጀክት ድርሻ ከፍተኛ ነው፡፡
የባህር ትራንስፖርትና የዓሳ ሀብት ልማት፡-
በ1,874 ስዄየር ኪሎ ሜትር ስፋት ላይ 74 ቢሊዮን ሜትር ኪዩቢክ የመያዝ አቅም ያለው ሰው ሠራሽ ሐይቅ ስለሚፈጠር በአካባቢው በታንኳ እና በጀልባ የትራንስፖርት አገልግሎት፣እንዲሁም ተጨማሪ የዓሳ ሀብት ለማልማት ዕድል ይፈጥራል፤ በዓለማችንም ተጠቃሽ የቱሪስት መዳረሻም ይሆናል፡፡
የውሃ፣ የየብስ እና የልዩልዩ ብዝሃ ህይወት መገኛ መሆን፡-
የሚፈጠረው ሐይቅ እና ደሴቶች ለብዙ የሐይቅ ዳር አዕዋፋት መስሕብ ይሆናል፤በዚህም በአካባቢው ነዋሪ ለሆኑትም ሆነ ከሌላ ቦታ ፈልሰው ለሚመጡ አዕዋፋት ተመራጭ የመኖሪያ ቦታ ይሆንላቸዋል፡፡
የኃይል ትስስር እና ሽያጭን ታሳቢ ማድረጉ፡-
ኘሮጀክቱ የሃገሪቱን የማመንጨት አቅም በማሳደግና የኃይል ኤክስፖርት ዕቅዱን ለማሳካት ከፍተኛ ድርሻ ያበረክታል፡፡
የካርቦን ዳይኦክሳይድ ልቀትን ማስወገድ፡-
የውሃ ኃይል ማመንጫ ከካርቦንዳይኦክሳይድ ልቀት ነፃ በመሆኑ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የአካባቢ ሥነ-ምህዳርንም በመጠበቅ ረገድ የሚያበረክተው አስተዋፅ ኦከፍተኛ ነው፡፡
ሰፊ የሥራ ዕድልና የዕውት ሽግግር መፍጠሩ፡-
በግንባታ ወቅት በርካታ ኢትዮጰያውያንና የተለያዩ ሀገራት ዜጎች ተሳትፈዋል፡፡ ኢትዮጵያውያን ዜጎችም ይህን በመሳሰሉት የፕሮጀክት ግንባታ ተግባራት ላይ ከፍተኛ ክህሎትና ልምድ ካላቸው ካደጉ ሃገራት ሙያተኞች ጋር አብሮ በመስራት በሚደረገው ጉልህ እንቅስቃሴዎች የዕውቀት፣ የአሰራር ልምድና ክህሎት እንዲቀስሙ ስለሚረዳ የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር በማስገኘቱ ረገድ ጉልህ ጠቀሜታም እያስገኘ ነው፡፡
ሥርዓተ ፆታን በተመለከተ፡-
በኘሮጀክቱ ግንባታ ወቅት ለወንዶች እና ለሴቶች እኩል የሥራ ዕድል ተፈጥሯል፡፡
የንግድ ዕድሎች መስፋፋት፡-
በኘሮጀክቱ መኖር ምክንያት የንግድ እንቅስቃሴ ዕድሎች በመስፋፋታቸው ሃገርንም ሆነ የአካባቢውን ህብረተሰብ ተጠቃሚ ማድረግ አስችሏል፡፡
የተሻለ ተደራሽነት መፍጠሩ፡-
ለኘሮጀክቱ የተለያዩ ክፍሎች መዳረሻ እየተገነቡ ያሉ አዳዲስ የገጠር መንገዶች ለተሽከርካሪ መዳረሻ ዕድል በመፍጠራቸው ለአካባቢው የትራንስፖርት መሻሻልን በመፍጠር የኘሮጀክቱን አካባቢ እና ዋና ዋና ከተሞችን በማገናኘት በኩል ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
ከግድቡ በታች ለሚገኙ ሃገራት የሚኖረው አካባቢያዊና ዓለም አቀፋዊ ፋይዳ፡-
አባይ ድንበር ተሻጋሪ ወንዝ ሲሆን ከኢትዮጵ ያተራራማ ቦታዎች ተነስቶ ወደሱዳን እና ግብፅ ይፈሳል፡፡ ሱዳን ድንበር ላይ የወንዙ ዓመታዊ አማካይ የፍሰት መጠን 50.6 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ነው፡፡ለተፋሰሱ ሃገራት ከሚያስገኘው ጠቀሜታ አንጻርም፡-
በሱዳን፡- የጎርፍን አደጋ መቀነሱ፣ የተመጣጠነ ውሃ ሁሌም እንዲኖር ማድረግ፣ ድርቅን መከላከል፣የውሃ ትነትንና የደለል መጠንን መቀነስ፣ ከግድቡ በታች ኃይል ማመንጨት አቅምን በማሳደግ ተጨማሪ የኤሌክትሪክ ኃይል የማግኘት ዕድል መፍጠር፡፡
በግብፅ፡- ውሃን በመቆጠብ የተሻለ ውሃ አጠቃቀም እንዲኖር ማድረጉ፣ ጎርፍ መከላከልና፣ሁሌም የተመጣጠነ ውሃ ማግኘት ማስቻሉ፣ የውሃ ትነትንና የደለል መቀነስ፣ለመጓጓዣና ተጨማሪ ኤሌክትሪክ ኃይል የማግኘት ዕድል መፍጠሩ፡፡
ለአካባቢና ዓለም አቀፋዊ ጠቀሜታ፡- የአየር ብክለትን በመቀነስ የአየር ንብረትን ለውጥ መቀነስ፣በአካባቢ አገሮች የኃይል ትስስርን በመፍጠር ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ማምጣት፡፡
በአጠቃላይ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በናይል ተፋሰስ አገራት የትብብር፣ የልማት፣የተሻለ ውሃ አጠቃቀም እንዲሁም ለአካባቢው አየር ንብረት መሻሻል ጉልህ ጠቀሜታ እንዳለው ይታመናል፡፡
የግንባታው ዋና ዋናክ ፍሎች፡-
ግድቡ 1‚780 ሜትር ርዝመት እና 145 ሜትር ከፍታ እንዲሁም የ RCC ሙሌት መጠኑ 10.2 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ያለው ሆኖ በአባይ ወንዝ እየገነባነው ያለ ግድብ ነው፡፡
የዋናው ግድብ ስራ አፈጻፀም እስካሁን ድረስ ከ8.1ሚሊዮንኪዩቢክ ሜትር ያላነሰ የRCC አርማታ ሙሌት ሥራ ተከናውኗል፡፡ ይህም ዝቅተኛ ሲሚንቶ የሚጠቀምና ወጪ ቆጣቢ ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ ነው፡፡ የፕሮጀክቱ ግንባታ ሁለት ዋና የወንዙን አቅጣጫ ማስቀየር ኩነቶች እና ተጓዳኝ ግንባታ ሂደቶችን ያለፈ ሲሆን፤ከግድቦቹ በስተኋላ የተጠራቀመውን ውሃ ወደ እያንዳንዱ የኃይል ማመንጫ ዩኒቶች የሚያደርሱ የብረት አሸንዳዎችና የታችኞችን ሃገራት የውሃ ፍላጎት ባገናዘበ መልኩ አገልግሎት የሚሰጡ ተጨማሪ ሁለት የቦተም አውትሌቶችም አሉት፡፡
ኃይል ማመንጫ ቤቶች ግንባታ