በሚኔሶታና ሚድዌስት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለህዳሴው ግድብ 40 ሺህ ዶላር አበረከቱ - መነሻ - am

Portlets aninhado

Publicador de Conteúdos e Mídias

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Sex, 17 jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Qua, 8 jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Qua, 8 jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Publicador de Conteúdos e Mídias

በሚኔሶታና ሚድዌስት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለህዳሴው ግድብ 40 ሺህ ዶላር አበረከቱ

በሚኔሶታና ሚድዌስት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ያሰባሰበውን የ40 ሺህ ዶላር ድጋፍ አስረከበ፡፡

የኮሚቴው ሰብሳቢ ቄስ ፍራንሲስ ኮሚቴው በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ የሚነዙ የተሳሳቱ ትርክቶችን ለመመከትና ለግድቡ ግንባታ የሚሆን ሃብት ለማሰባሰብ መመስረቱን ገልጸዋል፡፡

ኮሚቴው ሁለተኛ 40 ሺህ ዶላር እያሰባሰበ መሆኑን ጠቅሰው፥ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሃብት ከማሰባሰብ ጎን ለጎን ከልዩ ልዩ አካላት ጋር በመተባባርና የአሜሪካ ምክር ቤት ተመራጮችን በማግባባት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስከብሩ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ስራዎችን እየሰራ ነው ብለዋል፡፡

በሚኔሶታ የኢፌዴሪ ቆንስል ጀነራል አምባሳደር አብዱላዚዝ መሐመድ በሚኔሶታና ሚድዌስት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለሃገራዊ ፕሮጀክቶችና ወቅታዊ ጥሪዎች ከፍተኛ ሃብት በማሰባሰብ የሃገር ባለውለታነታቸውን ማረጋገጣቸውን ጠቅሰዋል፡፡

በአካባቢው የሚኖሩ የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በዚህ ሳይወሰኑ በፐብሊክ ዲፕሎማሲና በሃገር ውስጥ የቀጥታ ኢንቨስትመንት እያሳዩት ያለው ተሳትፎም የሚበረታታ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ዳያስፖራው እያደረገ ላለው አበረታች እንቅስቃሴ አመስግነው፥ ዳያስፖራው ከጊዜያዊ ልዩነት ይልቅ ለሃገራዊ አንድነት እንዲሰራ ጠይቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት በበኩላቸው ዳያስፖራው፥ በኮቪድ19 ምክንያት ችግር ውስጥ ሆኖ ሃገሩን ለማገዝ እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ማቅረባቸውን ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ዋና ዳይሬክተሯ አያይዘውም ወቅቱ ዳያስፖራው ከመቼውም ጊዜ በላይ አንድነቱን አጠናክሮ ለሃገሩ የሚቆምበት ወቅት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ኤፍ ቢ ሲ

Portlets aninhado

Publicador de Conteúdos e Mídias

— 5 Itens por página
Exibindo 1 - 5 de 16 resultados.