የህዳሴ ግድብ ግንባታ የተጀመረበት 10ኛ ዓመት በጁባ ተከበረ - መነሻ - am

Portlets aninhado

Publicador de Conteúdos e Mídias

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Sex, 17 jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Qua, 8 jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Qua, 8 jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Publicador de Conteúdos e Mídias

የህዳሴ ግድብ ግንባታ የተጀመረበት 10ኛ ዓመት በጁባ ተከበረ

የህዳሴ ግድብ ግንባታ የተጀመረበት 10ኛ ዓመት ክብረ-በዓል የሃይማኖት አባቶች፣ በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላት እና በተለያዩ ዓለምአቀፍ ተቋማት ውስጥ የሚሠሩ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በጁባ ተከብሯል።
በደቡብ ሱዳን የኢፌዴሪ አምባሳደር ነቢል ማህዲ በደቡብ ሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን ለህዳሴ ግድብ ግንባታ፣ በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ጁንታው የፈጸመው ጥቃትን ተከትሎ ለሠራዊቱ በተደረገው የገንዘብ ድጋፍ፣ ለገበታ ለሀገር ፕሮጀክት እና ለሌሎችም ሃገራዊ ጥሪዎች ለተሰጡ ምላሾች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
አያይዘውም የህዳሴ ግድብ የሁሉም ኢትዮጵያውያን አልፎም የአፍሪካ ፕሮጀክት ነው ያሉት አምባሳደሩ፥ ኢትዮጵያ ከታችኞቹ የተፋሰስ ሃገራት ጋር ያላትን ልዩነት በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት አፍሪካዊ መፍትሔ እንዲያገኝ እየሠራች መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በደቡብ ሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን እስካሁን ድረስ ለህዳሴ ግድብ ግንባታ 600 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ያህል በቦንድ ግዥና በስጦታ ማበርከታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
ተሳታፊዎችም ለግድቡና ለሌሎችም የልማት ፕሮጀክቶች የሚያደርጉትን ድጋፍ በቀጣይነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡
ኤፍ ቢ ሲ

Portlets aninhado

Publicador de Conteúdos e Mídias

— 5 Itens por página
Exibindo 1 - 5 de 16 resultados.