ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ተማሪዎች በህዳሴ ግድብና በውጭ ጣልቃ ገብነት ላይ ያተኮረ የበይነ መረብ ውይይት አካሂደዋል፡፡ - መነሻ - am

Portlets aninhado

Publicador de Conteúdos e Mídias

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Sex, 17 jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Qua, 8 jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Qua, 8 jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Publicador de Conteúdos e Mídias

ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ተማሪዎች በህዳሴ ግድብና በውጭ ጣልቃ ገብነት ላይ ያተኮረ የበይነ መረብ ውይይት አካሂደዋል፡፡

በአርሲ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት ከስምንት ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ የተማሪ ህብረት ተወካዮች ተሳትፎ ያደረጉበት የበይነ መረብ ውይይት አድርገዋል፡፡
በዚህም ውይይት የህዳሴ ግድብ ላይ የተማሪዎች ሚና፣የውጪ ጣልቃ ገብነት እንዴት መቋቋም ይቻላል እንዲሁም 6ተኛ አገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከተማሪዎች ምን ይጠበቃል በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ማድረጋቸው ተገልጿል።
የአርሲ ዩኒቨርሲቲ አለምአቀፍ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ዶክተር ገመዳ ሁንዴ÷ምክክሩ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ሉዓላዊነትን በተመለከተ ድምፅ ለማሰማት ያለመ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡
ተማዎች ሰላም ከማስጠበቅ አንፃር በተቋሙ የበለጠ እየሰሩ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ ለህዳሴ ግድብ ግንባታ ድጋፍ እያደረጉ ነው ማለታቸውን ሪፖርተራችን ሊያ ዱጉማ ዘግባለች።
በተመሳሳይም “ድምፃችን ለነፃነታችንና ለሎአላዊነታችን” በሚል ቃል የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ውይይት አድርገዋል።
በውይይታቸውም ያለችን ሀገር አንድ ናትና አባቶቻችን ሎአላዊት ሀገር እንዳስረከቡን እኛም ለልጆቻችን በማንም ጣልቃ ገብነት የማትደናቀፍ ሀገር ማውረስ እንፈልጋለን ብለዋል።
የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ከአገር አቀፍ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ጋር ነው በበይነ-መረብ የአንድነት ድምፅ ያሰሙት።
የመርሐ ግብሩ አዘጋጅ ሀገር አቀፍ የተማሪዎች ህብረትና የኢትዮጵያ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከአርባ አምስቱ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር ነው።
የውይይት መርሐ ግብሩ በዋናነት በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር አዳራሽ ሲሆን አርባ አምስቱ ዩኒቨርሲቲዎች ከያሉበት በበይነ መረብ ተሳታፊ ሆነዋል።
በውይይቱ ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፣ ስለ ውጭ ሀገራት ጣልቃ ገብነት ፣ ስለ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫና ከኮሮና ቫይረስ መከላከል በስፋት ተነስቷል።
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሕብረት ፕሬዝዳንት ተማሪ ነብዩ ተገኝ÷በ ውይይቱ ወቅት በተነሱ ርዕሰ ጉዳዮች ሀሳቡን ሲያጋራ የህዳሴው ግድብ ለእኛ ተስፋችንና እንደ አይን ብሌናችን እንቆጥረዋለን ነው ያለው።
ተማሪ ነብዩ በዩኒቨርሲቲው 38 ሺህ ተማሪዎች መኖራቸውን ጠቁሞ ሁሉም ተማሪ በ8100 ላይ እንዲሳተፉ እያስተባበሩ መሆኑንም ተናግሯል።
የኮሮና ወረርሽኝ ለመከላከልም ተማሪዎችን ጨምሮ ሁሉም የግቢው ማህበረሰብ ጥብቅ ጥንቃቄ ያደርጋሉ ብሏል።
በውይይቱ የተማሪ ሕብረት አመራሮች፣ የሴት ተማሪ ተወካዮች ፣ የአካል ጉዳተኛ ተማሪ ተወካዮችና ሌሎችም ተማሪዎች መሳተፋቸውን ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡

Portlets aninhado

Publicador de Conteúdos e Mídias

— 5 Itens por página
Exibindo 1 - 5 de 16 resultados.