በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ1ቢሊየን ብር በላይ ተሰበሰበ - display page
Publicador de Conteúdos e Mídias
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ1ቢሊየን ብር በላይ ተሰበሰበ
ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ድጋፍ ከሐምሌ 1/2013 እስከ ሰኔ 30/2014 ዓ.ም 1ቢሊየን 186ሚሊዮን 297 ሺህ 461ብር ተሰብስቧል፡፡
ድጋፉ የተሰበሰበው ከሀገር ውስጥ ቦንድ ሽያጭና ስጦታ፣ከዲያስፖራ ቦንድ ሽያጭና ስጦታ፣በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ስጦታ አካውንት ገቢ፣ ከፒን ሺያጭ ገቢና ከ8100 አጭር የሞባይል ስልክ መልዕክት አገልግሎት ነው፡፡
የግድቡ ግንባታ ከተጀመረበት 2003 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30/2014 ዓ.ም ድረስ ከሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ከሚገኙ የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት እንዲሁም ከልዩ ልዩ ገቢዎች በአጠቃላይ 16 ቢሊዮን 915ሚሊዮን 312ሺህ 137 ብር መሰብሰቡም ታውቋል፡፡