ጠ/ሚ ዐቢይ በህዳሴ ግድብ የመረጃ ልውውጥ ላይ ትኩረት ባደረገ ስብሰባ ላይ ተሳተፉ - መነሻ - am
Geneste portlets
Contentverzamelaar
Statistics
× አድራሻ: ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስኩየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር
Webcontent zoeken
Contentverzamelaar
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መረጃ ልውውጥ ላይ ትኩረቱን ባደረገ ስብሰባ ላይ ተሳተፉ፡፡
በበይነ መረብ የተካሄደው ስብሰባ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት እና የአፍሪካ ህብረት የወቅቱ ሊቀ መንበር ፌሊክስ ሺሴኬዲ የተዘጋጀ ሲሆን፥ በህዳሴ ግድብ ላይ መረጃ መለዋወጥን አላማው ያደረገ ነው፡፡
ሊቀ መንበሩ በዚህ ወቅት የአፍሪካ ጉዳዮች በህብረቱ ስር እንደሚቆዩ ጠቅሰው፥ ሁሉም አካላት በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር የሚያደርጉትን ድርድር መቀጠል ይገባቸዋል ብለዋል፡፡
በስብሰባው ላይ ፕሬዚዳንት ፊሊክስ ቲሼኬዲ ጉዳዩን አስመልክቶ በተገቢው ሰዓት ሙሉ ሪፖርቱን እንደሚያቀርቡ እና ውይይቱ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
የአፍሪካ ጉዳይ በአፍሪካ ህብረት በኩል ሊፈታ እንደሚገባ ሊቀመንበሩ እንዳሰመሩበትም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የትዊተር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ምንጭ፡- ኤፍ ቢ ሲ ፣ ሰኔ 17 ፣ 2013
Geneste portlets
Contentverzamelaar
— 5 artikelen per pagina