"በታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ ላይ የሚካሄደው የሶስትዮሽ ድርድር አሁንም ቢሆን በአፍሪካ ህብረት አስተባበሪነት እንዲቀጥል የኢትዮጵያ ጽኑ ፍላጎትት ነው" የውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር - መነሻ - am

Geneste portlets

Contentverzamelaar

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ vr, 17 jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች wo, 8 jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ wo, 8 jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Contentverzamelaar

"በታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ ላይ የሚካሄደው የሶስትዮሽ ድርድር አሁንም ቢሆን በአፍሪካ ህብረት አስተባበሪነት እንዲቀጥል የኢትዮጵያ ጽኑ ፍላጎትት ነው" የውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር
(ኢ ፕ ድ)
በታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ ላይ የሚካሄደው የሶስትዮሽ ድርድር አሁንም ቢሆን በአፍሪካ ህብረት አስተባበሪነት እንዲቀጥል ኢትዮጵያ ጽኑ ፍላጎትት እንዳላት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል-አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለፁ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል-አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለመገናኛ ብዙኃን ሳምንታዊ የፕሬስ መግለጫ ሰጥተዋል።
አምባሳደር ዲና ፖለቲካ ዲፕሎማሲ፣ የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ድርድር፣ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲና የዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲን የተመለከቱ ጉዳዮችን በመግለጫቸው ዳስሰዋል።
ከፖለቲካ ዲፕሎማሲ አኳያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን፡-
•ከሩሲያ-አፍሪካ የትብብር ፎረም ዋና ጸሐፊ ክቡር አምባሳደር ኦሌግ ኦዜሮቭን ጋር ባደረጉት ውይይት እ.ኤ.አ በ2022 የሚካሄደውን ሁለተኛው የአፍሪካ-ሩሲያ ጉባኤ እንዲሁም የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ማጠናከር በሚቻልበት ዙሪያ ምክክር ማድረጋቸው ገልጸወዋል።
•ከቬትናም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከክቡር ቡይ ታን ሰን ጋር የስልክ ውይይት አድርገዋል። በሁለቱ አገራት መካከል የተጀመረውን 45ኛ ዓመት የዲፕሎማሲ ግንኙነት በማስመልከት፤ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እንዲሁም በባለብዙ መድረኮችም ለመተባበር ምክክር አድርገዋል።
•በተለያዩ አገራት የሚገኙ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ አምባሳደሮች ተቀማጭ በሆኑባቸው አገራት የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ የማስጨበጥ እና የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ለማጠናከር የሚያስችል ውይይቶችን አካሂደዋል።
በዚህ መሰረትም፡-
•በጀርመን የኢፌዲሪ አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን በጀርመን ከሚገኙ ምሁራን፣ ሀሳብ አፍላቂዎችና ተመራማሪዎች ጋር የቤይነ መረብ ውይይት አካሂደዋል።ውይይቱ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች በተለይም በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ፣ ታላቁ የኢትዮጵ ህዳሴ ግድብ ድርድር፣ የኢትዮ-ሱዳን የድንበር ጉዳይ እንዲሁም 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ ያተኮረ ውይት አካሂደዋል።
•በኡጋንዳ ክብርት አምባሳደር አለምፀሃይ መሰረት ከኡጋንዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ከክቡር ኦርየም ኦከሎ ጋር ውይይት አድርገዋል። በውይይታቸውም አምባሳደር አለምጸሀይ በታላቁ የህዳሴ ግድብና በወቅታዊ አገራዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
•በደቡብ ሱዳን አምባሳደር ነቢል መሃዲ ከደቡብ ሱዳን የመከላከያ ሚኒስትር ጋር በሁለትዮሽና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ፡፡ ሚኒስትሩም ኢትዮጵያ በቀጠናው ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር እያደረገች ያለውን ጠንካራ ስራ ደቡብ ሱዳን በደንብ እንደምትገነዘብ ተናግረዋል፡፡
•በሶማሊያ የተሹሙት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አብዱልፈታህ አብዱላሂ የሹመት ደብዳቤያቸውን ቅጂ ለአገሪቱ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ጉዳዮች ሚኒስትር ማቅረባቸውን ገልጸዋል።
•በኡጋንዳ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕክተኛእና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አለምፀሃይ መሰረት ከኡጋንዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ከክቡር ኦርየም ኦከሎ ጋር ውይይት አድርገዋል። በውይይታቸውም አምባሳደር አለምጸሀይ በታላቁ የህዳሴ ግድብና በወቅታዊ አገራዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ ማብራሪያ መስጠታቸውን ገልጸዋል።
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ፣
•የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር አስመልክቶ በሱዳን በኩል ለቀረበው ሃሳብ፣ የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ቢሮ ስብሰባ እንዲያካሂድ በወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ-መንበር በኩል ጥሪ እንዲደረግ ኢትዮጵያ ሀሳብ መጠየቋን ገልጸዋል፡፡
•ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ መርህ መሰረት በጉዳዩ ላይ ሲደረግ የነበሩ ድርድሮች ውጤት የተገኘባቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በውሃ አሞላል ላይ ትኩረት ተደርጎ ድርድር እንዲካሄድ የኢትዮጵያ ፍላጎት መሆኑን ጠቅሰው፤ በግብፅና ሱዳን በኩል በተደጋጋሚ ከድርድሩ አቋርጦ መዉጣት ሂደቱን ያዘገየ መሆኑን አስረድተዋል። የድርድሩም ውጤት በዋናነት በሶስቱ አገሮች መካከል ሆኖ የአፍሪካ ህብረት መሪነት እንዲቀጥል ኢትዮጵያ በጽኑ እንደምታምን አስገንዝበዋል፡፡
•በታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ ላይ የሚካሄደው የሶስትዮሽ ድርድር አሁንም ቢሆን በአፍሪካ ህብረት አስተባበሪነት እንዲቀጥል ኢትዮጵያ ጽኑ ፍላጎትት እንዳላት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በደብዳቤያቸው መግልጻቸውን አንስተዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል-አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የሰጡት ሳምንታዊ የፕሬስ መግለጫ፣
==================
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል-አቀባይ ክቡር አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ፤ ሚያዝያ 19 ቀን 2013 ዓ.ም ለመገናኛ ብዙኃን ሳምንታዊ የፕሬስ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸው በፖለቲካ ዲፕሎማሲ፣ የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ድርድር፣ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ እንዲሁም የዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲን የተመለከቱ ጉዳዮችን ዳስሰዋል።
1. ከፖለቲካ ዲፕሎማሲ አኳያ፡-
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን፡-
•ከሩሲያ-አፍሪካ የትብብር ፎረም ዋና ጸሐፊ ክቡር አምባሳደር ኦሌግ ኦዜሮቭን ጋር ባደረጉት ውይይት እ.ኤ.አ በ2022 የሚካሄደውን ሁለተኛው የአፍሪካ-ሩሲያ ጉባኤ እንዲሁም የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ማጠናከር በሚቻልበት ዙሪያ ምክክር ማድረጋቸው ገልጸወዋል።
•ከቬትናም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከክቡር ቡይ ታን ሰን ጋር የስልክ ውይይት አድርገዋል። በሁለቱ አገራት መካከል የተጀመረውን 45ኛ ዓመት የዲፕሎማሲ ግንኙነት በማስመልከት፤ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እንዲሁም በባለብዙ መድረኮችም ለመተባበር ምክክር አድርገዋል።
•በተለያዩ አገራት የሚገኙ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ አምባሳደሮች ተቀማጭ በሆኑባቸው አገራት የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ የማስጨበጥ እና የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ለማጠናከር የሚያስችል ውይይቶችን አካሂደዋል።
በዚህ መሰረትም፡-
•በጀርመን የኢፌዲሪ አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን በጀርመን ከሚገኙ ምሁራን፣ ሀሳብ አፍላቂዎችና ተመራማሪዎች ጋር የቤይነ መረብ ውይይት አካሂደዋል።ውይይቱ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች በተለይም በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ፣ ታላቁ የኢትዮጵ ህዳሴ ግድብ ድርድር፣ የኢትዮ-ሱዳን የድንበር ጉዳይ እንዲሁም 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ ያተኮረ ውይት አካሂደዋል።
•በኡጋንዳ ክብርት አምባሳደር አለምፀሃይ መሰረት ከኡጋንዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ከክቡር ኦርየም ኦከሎ ጋር ውይይት አድርገዋል። በውይይታቸውም አምባሳደር አለምጸሀይ በታላቁ የህዳሴ ግድብና በወቅታዊ አገራዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
•በደቡብ ሱዳን አምባሳደር ነቢል መሃዲ ከደቡብ ሱዳን የመከላከያ ሚኒስትር ጋር በሁለትዮሽና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ፡፡ ሚኒስትሩም ኢትዮጵያ በቀጠናው ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር እያደረገች ያለውን ጠንካራ ስራ ደቡብ ሱዳን በደንብ እንደምትገነዘብ ተናግረዋል፡፡
•በሶማሊያ የተሹሙት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አብዱልፈታህ አብዱላሂ የሹመት ደብዳቤያቸውን ቅጂ ለአገሪቱ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ጉዳዮች ሚኒስትር ማቅረባቸውን ገልጸዋል።
•በኡጋንዳ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕክተኛእና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አለምፀሃይ መሰረት ከኡጋንዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ከክቡር ኦርየም ኦከሎ ጋር ውይይት አድርገዋል። በውይይታቸውም አምባሳደር አለምጸሀይ በታላቁ የህዳሴ ግድብና በወቅታዊ አገራዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ ማብራሪያ መስጠታቸውን ገልጸዋል።
1.1 የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ፣
•የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር አስመልክቶ በሱዳን በኩል ለቀረበው ሃሳብ፣ የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ቢሮ ስብሰባ እንዲያካሂድ በወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ-መንበር በኩል ጥሪ እንዲደረግ ኢትዮጵያ ሀሳብ መጠየቋን ገልጸዋል፡፡
•ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ መርህ መሰረት በጉዳዩ ላይ ሲደረግ የነበሩ ድርድሮች ውጤት የተገኘባቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በውሃ አሞላል ላይ ትኩረት ተደርጎ ድርድር እንዲካሄድ የኢትዮጵያ ፍላጎት መሆኑን ጠቅሰው፤ በግብፅና ሱዳን በኩል በተደጋጋሚ ከድርድሩ አቋርጦ መዉጣት ሂደቱን ያዘገየ መሆኑን አስረድተዋል። የድርድሩም ውጤት በዋናነት በሶስቱ አገሮች መካከል ሆኖ የአፍሪካ ህብረት መሪነት እንዲቀጥል ኢትዮጵያ በጽኑ እንደምታምን አስገንዝበዋል፡፡
•በታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ ላይ የሚካሄደው የሶስትዮሽ ድርድር አሁንም ቢሆን በአፍሪካ ህብረት አስተባበሪነት እንዲቀጥል ኢትዮጵያ ጽኑ ፍላጎትት እንዳላት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በደብዳቤያቸው መግልጻቸውን አንስተዋል።
1.2 የትግራይ ወቅታዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ፣
•ኢትዮጵያ መንግሰት በትግራይ ክልል እደረገ ያለውን ሰብአዊ ድጋፍ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ም/ቤት ዕውቅና መስጠቱ፤ ለየኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ያለውን አቋም መግለጹን አብራርተዋል።
•የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮምሽን ከተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮምሽን ጋር የጋራ ምርመራ ለማድረግ መወሰኑ፣ እንዲሁም ከአፍሪካ የሰዎችና እና የሰብዓዊ መብት ኮምሽን ጋር የጋራ ምርመራ እንዲያደርጉ ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን በም/ቤቱ በአዎንታዊነት መነሳቱን ገልጸዋል።
•በጠቅላይ አቃቢ ህግ እና በፌደራል ፖሊስ በኩል ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን፣ አጥፊዎች በህግ ተጠያቂ ለማድረግ መንግሰት ቁርጠኛ መሆኑን፤
•በክልሉ ቀድም ሲል ሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽ ያልነበሩ የተወሰኑ ቦታዎች ተደራሽ አሁን ማድረስ የተቻለ መሆኑን አብራርተዋል።
2.ኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ አኳያ፣
•የኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ፂዮን ተክሉ የኢትዮጵያን የቱሪስት መስህቦች በኬንያ የሚያስተዋውቅ የበይነ መረብ የፓናል ውይይት ላይ ተሳትፈዋል። በወቅቱም የኢትዮጵያ አያሌ የቱሪስት መስህቦችን ለኬንያ ገበያ ተደራሽ ለማድረግ መንግስት የተለያዩ የማሻሻያ ስራዎችን እየሰራ መሆኑንም ገልፀዋል።
•በኳታር የሚገኘው ፓዎር ኢንተርናሽናል ሆልድንግ (PIH) ኩባንያ በአገራችን በግብርና፣ በመሰረተ ልማት፣ በተመጣጣኝ ዋጋ የመኖሪያ ቤት ልማት እንዲሁም በቱሪዝም ዘርፍ ድርጅታቸው ለመሰማራት ይችል ዘንድ የቅድመ-ኢንቬስትመንት ስብሰባ በኤምባሲው አስተባባሪነት መካሄዱ፣
•በሩስያ፣ ሴንትፒተርስ ’New Rules of the Growth” በሚል በተካሄደው ዓለም ዓቀፍ ልማት ላይ ያተኮረ የቢዝነስ ፎረም ላይ በመገኘት ክቡር አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ በአገራችን በንግድና በኢንቨስትመንት ለመሳተፍ ስላለው ምቹ ሁኔታን በተመከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
•በኦማን ሱልጣኔት በማዕድን ፍለጋ፣ ቁፋሮ፣ ማውጣት እና ማልማት መስከረ የተሰማራው ዩናይትድ ቢዝነስ-ገልፍ ፖታሽ ኮርፖሬሽን፤ በአገራችን የፓታሽ ማውጣት እና ማልማት ላይ ፍላጎት እንዳለው አሳውቋል።
3. ከአቅም ግንባታ አኳያ፣
•በኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሐመድ እንድሪስ የተመራው የልዑካን ቡድን በአዉሮፓ ክለስተር በታቀፉ 13 ሚሲዮኖች ውስጥ ለሚገኙ የሚሲዮን መሪዎች፣ ዲፕሎማቶችና የአይሲቲ ባለሙያዎች የዳያስፖራ ዳታቤዝ አጠቃቀምን በተመለከተ ስልጠና ሰጥቷል። በወቅቱ የተሰጡ ግብዓቶን በማካተት ዳታቤዙ በአጭር ግዜ ውስጥ ወደ ሙሉ ትግበራ ይጠበቃል።
4.ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ዘርፍ፣
•በአውሮፓ አንዳንድ የፓርላማ አባላትና መንግስታት እያስተጋቡ ያሉትን የተዛባ መረጃ ለመከላከል በዲፕሎማሲ እና በሎቢ፣ በማህበራዊና በአለምአቀፍ ሚዲያዎች እየተሰራጨ ያለውን ሀሰተኛ መረጃ ለማረምና በሎጅስቲክስ ማሰባሰብ ላይ ያተኮረው ግብረ ሀይል በመንግስት ላይ ያነጣጠሩ አሉታዊ ጫናዎችን በመቀነስ ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ የጀመረውን ሁለገብ የለውጥ ሂደት ለማገዝ ያለመ “ለኢትዮጵያ ሞጋች / Defend Ethiopia" የሚል ቡድን ተቋቁሟል።
•በቴል አቪብ የሚገኘው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ የኢትዮጵያ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ አስረኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ከኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን(ከቤተ እስራኤላዊያን ማህበረሰብ) ውይይት አካሄዷል።በወቅቱም ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን (ቤተ እስራኤላዊያን ማህበረሰብ) ድጋፋቸውን አጠናክረው ለመቀጠል ቃል ገብተዋል። እስካሁንም ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን(ቤተ እስራኤላዊያን ማህበረሰብ) ለማድረስ ከአንድ ሚሊዮን ዶላር በላይ የቦንድ ግዥ ፈጽምዋል።የተሰኘ የኢትዮጵያዊያን ግብረ ሀይል በአውሮፓ ተቋቋሟል።
•በካናዳ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ ከጥምረት ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በካናዳ ጋር በመተባበር በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ወቅታዊ የመረጃ ልውውጥ ለማድረግ እንዲሁም የቦንድ ግዥን አስመልክቶ መረጃ ለመስጠት ያለመ የቤይነ መረብ ውይይት አካሂዷል።በመድረኩ በክብር እንግድነት የተሳተፉት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውሃ፣መስኖ እና ኢነርጅ ሚኒስትር ዶ/ር ስለሽ በቀለ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የአገራችን በነጻነት የመልማት መብት በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአንድነት እና በመግባባት በጋራ በመቆም ከዳር እስከ ዳር ሊደግፈው እንደሚገባ እንዲሁም ዳያስፖራው የግድቡ አምባሳደር በመሆን የአገሩን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እና መብት ለማሳወቅ እንዲረባረብ ጥሪ አቅርበዋል።
•በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ የተመራ የልዑካን ቡድን ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በተያዩ ርዕሰ ጉዳዩች ላይ ውይይት አድርጓል። በሳምንቱም የዚሁ አካል የሆነውና በኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት የተመራ ውይይት በሲያትልና ሎስ አንጀለስ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ተካሂዷል። በወቅቱም በወቅታዊ አገራዊ ሁኔታዎች ላይ ገለጻ ተሰጥቷል።ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንም ለአገራቸው በተለያየ ዘርፍ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በውይይቱ ወቅት ገልጸዋል።
•በተለያዩ አገሮች በችግር ላይ የነበሩ ዜጎቻችን ወደ አገር ቤት የመመለስ ስራ ተከናውኗል። በዚህም ከሳዑዲ አረቢያ ከጂዳ 592፣ ከሪያድ 339፣ 16 ከፑንትላንድ በድምሩ 947 ዜጎች ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡

— 5 artikelen per pagina
Toont 1 - 5 van 16 resultaten.