‹‹የግብጽ ጩኸት ኢትዮጵያ ከበለጸገች የአፍሪካ የኃይል ሚዛን ወደሷ ያጋድላል ከሚል ሥጋት ይመነጫል›› – ፕሮፌሰር ተሰማ ዘውዱ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት - መነሻ - am

Geneste portlets

Contentverzamelaar

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ vr, 17 jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች wo, 8 jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ wo, 8 jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Contentverzamelaar

‹‹የግብጽ ጩኸት ኢትዮጵያ ከበለጸገች የአፍሪካ የኃይል ሚዛን ወደሷ ያጋድላል ከሚል ሥጋት ይመነጫል›› – ፕሮፌሰር ተሰማ ዘውዱ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት
ደባርቅ:- የግብጽ ጩኸት ኢትዮጵያ ካደገችና ከበለጸገች የአፍሪካ የኃይል ሚዛን ስለሚያጋድል ተቀባይነትና ተደማጭነት አጣለሁ ከሚል ስጋት የመነጨ እንደሆነ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ተሰማ ዘውዱ አስታወቁ።
ፕሮፌሰር ተሰማ ዘውዱ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለፁት፤ የግብጽ ጩኸት ኢትዮጵያ ካደገችና ከበለፀገች የአፍሪካ የኃይል ሚዛን ወደ ኢትዮጵያ ስለሚያጋድል ተቀባይነትና ተደማጭነት አጣለሁ ከሚል ስጋት የሚመነጭ እንጂ ውሃ አጥታ አይደለም።
ግብጽ ለበርካታ ዓመታት የሚያገለግላት ውሃ በከርሰ ምድር አስቀምጣለች፣ በነፍስ ወከፍ ደረጃ ያላት የውሃ ክምችት ከኢትዮጵያ በላይ ነው፣ ከፍተኛ የመብራት አገልግሎት ተጠቃሚ መሆኑዋንም አመልክተዋል።
የኃይል ሚዛኑን ለማስጠበቅ ኢትዮጵያዊያን የውስጥ ችግራቸውን በመፍታት በጋራ ሊቆሙ እንደሚገባም ያመለከቱት ፕሮፌሰሩ፣ ‹‹የግድቡ መጠናቀቅ አሁን የምንጣላበትንና የምንጋጭበት ችግር ሁሉ ሊቀርፍ ይችላል›› ብለዋል።
የህዳሴው ግድብ በከፍተኛ የጥራት ደረጃ የሚሰራ ነው፣ ግድቡ ከተጠናቀቀ በኋላ ሌሎች ግድቦችን ለመሥራት መዘጋጀት ያስፈልጋል ያሉት ፕሮፌሰሩ፣ የውሃ ሀብታችንን በፍትሀዊነት የመጠቀም መብት እንዳለን አስታውቀዋል።
ከ85 በመቶ በላይ ውሃው ከኢትዮጵያ እየፈሰሰ የግብጽን የልብ ትርታ ተከትሎ የሚሰራ መሆን ያለበት፡፡ የአካባቢውን ተጠቃሚነት ከግምት አስገብቶ መገንባት የኢትዮጵያ መብት ነው። በእዚህ ሁኔታ ውሃው የግብጽ ቢሆን ኖሮ አንድም ኩባያ ውሃ አያስቀዱንም ነበር ብለዋል።
በአሁኑ ጊዜ በተለይ ወደፊት አንድ ኩባያ ውሃ ከነዳጅ በላይ ውድ ሊሆን የሚችልበት አጋጣሚ ሰፊ ነው ያሉት ፕሮፌሩ፣ ምክንያቱም ነዳጅ እየጠፋ ስለሚሄድ ወደፊት ነዳጅ የሚጠቀሙ በሙሉ በታዳሽ ኃይል የሚሰሩበት አጋጣሚ ይመጣል፣ ስለዚህ የውሃ ሀብት በቀላሉ አይታይም ብለዋል፡፡
የውስጥ ችግራችንን ፈትተን በግድብ ግንባታ ላይ ተረባርበን በማጠናቀቅ ወደ ሌሎች ግንባታዎች መሄድ ያስፈልጋል እንጂ የውጭ ሃይሎች የሚሰጡንን አጀንዳ ተቀብለን መጋጨት እንደሌለብን አመልክተዋል።
እንደርሳቸው ማብራሪያ፤ የጀመርነውን ግድብ እንዳንጨርስ ከፍተኛ ጫናዎች አሉ፣ ጫናዎች ቢበረቱም ግድቡ መሞላቱ ስለማይቀር ማሰብ ያለብን ደልልን መከላከልና የአካባቢውን ሥነ ምህዳር መጠበቅ ላይ ነው።
ግድቡ ተሰርቶ ከማለቁ በፊት የኤሌክትሪክ ኃይሉን ወደሚፈለገው ቦታ ለማድረስ መሰረተ ልማቶች ተሰርተው መጠናቀቅ እንዳለባቸው ጠቁመው፣ ለበርካታ ዓመታት ከፍተኛ መስዋትነት የከፈልንበት ፕሮጀክት መጨረሻ ላይ ብክነት ላይ መዋል ስለሌለበት ቀድሞ ዝግጅት መደረግ እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።
ሞገስ ጸጋዬ
አዲስ ዘመን

Geneste portlets

Contentverzamelaar

— 5 artikelen per pagina
Toont 1 - 5 van 16 resultaten.