‹‹ልማቱ ትርጉም እንዲኖረው ሰው በህይወት የመኖር ተስፋው ሊለመልም ይገባል›› - መነሻ - am

Geneste portlets

Contentverzamelaar

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ vr, 17 jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች wo, 8 jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ wo, 8 jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Contentverzamelaar

‹‹ልማቱ ትርጉም እንዲኖረው ሰው በህይወት የመኖር ተስፋው ሊለመልም ይገባል››

ኢንጂነር ጌድዮን አስፋው የኢትዮጵያ ኤክስፐርቶች ቡድን ሰብሳቢና
የህዳሴ ግድብ ተደራዳሪ ኮሚቴ አባል
በአስቴር ኤልያስ
አዲስ አበባ፡- በተለያየ አቅጣጫ የሚካሄደው ልማት ትርጉም እንዲኖረው ሰው በህይወት የመኖር ተስፋው ሊለመልም እንደሚገባ የኢትዮጵያ ኤክስፐርቶች ፓናል ሰብሳቢና የአባይ ውሃ ጉዳይ ተደራዳሪ ኢንጂነር ጌድዮን አስፋው አመለከቱ።
ኢንጂነር ጌድዮን በተለይ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ እንዳስታወቁት፤ ከሁሉም በላይ መቅደም ያለበት የሰው ደህንነት ነው፤ ሰው በህይወት የመኖር ተስፋ ሲኖረው ልማቱም ትርጉም ይኖረዋል።
የኢትዮጵያ ህዝብ ቅድሚያ የሚሰጠውና መስጠትም ያለበት ለእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ደህንነት ነው ያሉት ኢንጂነር ጌድዮን፣ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በህገ መንግሥቱም እንደተደነገገው በህይወት የመኖር መብት አለው። የእያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ ህይወት በአስተማማኝ ሁኔታ መጠበቅ ካልቻልን ሌላ ትልቅ ነገር ለመሥራት በጣም እንቸገራለን ብለዋል።
እኔ በግሌ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ በሀገር ውስጥ ያለው አለመረጋጋት ለሁላችንም እንደስጋት የምንቆጥር በመሆኑ ሁላችንም ተባብረን ማቆም አለብን ያሉት ኢንጂነር ጌድዮን፣ በማንኛውም መልክ የውጭ ኃይልን ለመቋቋም የሚቻለው የውስጥ ጥንካሬና አንድነት ሲኖር እንደሆነ አመልክተዋል።
የውስጥ ጥንካሬና አንድነት በሌለበት ሁኔታ በተለያየ መልክ ኢትዮጵያ ላይ የሚሰነዘሩ ተቃውሞዎችን ለመቋቋም በጣም አስቸጋሪ ነው። ኢትዮጵያ እንደህዳሴ ግድብ ያሉ እና ሌሎችንም ትልልቅ ፕሮጀክቶች በምትሠራበት ወቅት የውስጥ ትብብሩ ወሳኝ እንደሆነ አስታውቀዋል።
ኢንጂነር ጌድዮን እንዳሉትም፤ በህዳሴ ግድቡ ሥራ የታየውን ቁርጠኝነት በሌሎች ተፋሰሶችም ለማስፋፋት እንዲሁም ሌሎች ፕሮጀክቶችን ለመሥራት ምልክት የሚሆነን ጥንካሬያችን ነው። ሌሎቹን ፕሮጀክቶች ለመሥራት አሁንም የውስጥ ጥንካሬ ያስፈልገናል። በውስጣችን አለመረጋጋት መኖሩ በጣም የሚያሳስብ ጉዳይ ሆኗል።
ሁላችንንም የሚያሳስበን ነገር ቢኖር እየታዩ ያሉ ችግሮች ናቸው፤ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል ያሉ ኢትዮጵያውያንን ደህንነት በመጀመሪያ መጠበቅ መቻል አለበት። በተለይም የውጪውን ተጽዕኖ ለመቋቋም በመጀመሪያ የውስጡን ማረጋጋትና አሁን ያለውን ሁኔታ መለወጥ ያስፈልጋል ብለዋል። ከደህንነት ጋር ተያይዞ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሁኔታ መቀየር እንዳለበትም አሳስበዋል።
በልማት በኩል ያለው ነገር ጥሩ ጅማሮ ሆኖ ሳለ ነገር ግን በሰው ደህንነትና በህይወት የመኖር ተስፋ የሚያጨለሙ ሁኔታዎችን መቀየር አለብን። እንደሱ ካልሆነ የምንሠራው ልማት ትርጉም አይኖረውም ብለዋል።

Geneste portlets

Contentverzamelaar

— 5 artikelen per pagina
Toont 1 - 5 van 16 resultaten.