የተዝካር ወጪ ለህዳሴ ግድብ! - መነሻ - am
Geneste portlets
Contentverzamelaar
Statistics
× አድራሻ: ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስኩየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር
Webcontent zoeken
Contentverzamelaar
በጀርመን ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ሌንሳ ተሾመ ከእናታቸው ሲስተር ፀሃይቱ ደስታ እና ሌሎች ልጆቻቸው ጋር በመመካከር ለአባታቸው አቶ ተሾመ ቦንጋሴ ወንታ 7ኛ ሙት ዓመት ተዝካር ወጪ ሊሆን የነበረ 100,000 ብር ለታላቁ ህዳሴ ግድብ አበርክተዋል።
ወይዘሮዋ ይህን ያደረጉት ከሁለት ልጆቻቸው ፊት ሲሆን ለዚህ ያነሳሳቸው ለሃገራቸው ያላቸው ፍቅር መሆኑን ተናግረው ሌሎችም ዜጎች በተመሳሳይ ለልደት፣ ለተዝካር እና ወዘተ ... የሚያወጡትን ወጪ ለግድቡ ቢያውሉ ትልቅ ማስታወሻ መሆኑን ተናግረዋል።
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ፤ የአቶ ተሾመ ቤተሰብ ያደረጉትን ድጋፍ በማመስገን ሁላችንም ኢትዮጵያውያን በዚህ መልኩ ታሪክ በመስራት የህዳሴ ግድባችንን አጠናቀን ሌሎች ግድቦችንም እንገነባለን ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
Geneste portlets
Contentverzamelaar
— 5 artikelen per pagina