ለሕዳሴ ግድቡ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ አስታወቁ፡፡ - መነሻ - am
Geneste portlets
Contentverzamelaar
Statistics
× አድራሻ: ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስኩየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር
Webcontent zoeken
Contentverzamelaar
በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለሕዳሴ ግድቡ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው መቀጠላቸውን አምባሳደር ፍጹም አረጋ አስታውቀዋል፡፡ አምባሳደሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት እንዳሉት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ብርሃን ለመስጠት በተቃረበበት ወቅት ከአሜሪካ የወገን ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል::
ለረጅም ጊዜ የቦስተን ነዋሪ የሆኑት አቶ ሰለሞን ለማ ከቤተሰባቸው ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ በኤምባሲው ተገኝተው 4ሺህ የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ አድርገዋል ነው ያሉት፡፡ 3ሺህ የአሜሪካ ዶላሩ በቦንድ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡
በግሬተር ፊለደልፊያ ነዋሪ የሆኑ ወገኖች በድምሩ 7ሺህ 400 የአሜሪካን ዶላር መለገሳቸውንም ገልጸዋል:: እስካሁን የተሰበሰበው ግማሽ ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወደ ሀገር ቤት ተላልፏልም ብለዋል አምባሳደሩ፡፡
ምንጭ፡- አሚኮ
Geneste portlets
Contentverzamelaar
— 5 artikelen per pagina