በድር ኢትዮጵያ ለህዳሴ ግድብ ግንባታ በአንድ የዙም ስብሰባ ከ50 ሺህ ዶላር በላይ አሰባሰበ - መነሻ - am
ネスティッドポートレット
アセットパブリッシャー
Statistics
× አድራሻ: ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስኩየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር
Webコンテンツの検索
アセットパブリッシャー
በድር ኢትዮጵያ (BADR ETHIOPIA) የተባለው ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ድርጅት ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በአንድ የዙም ስብሰባ ብቻ ከ50 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በላይ በስጦታ ማሰባሰቡን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ አስታውቀዋል፡፡
ይህ የሆነው “ግድቡ የኔ ነው” በሚል መሪ ቃል በአሜሪካ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመተባበር በተዘጋጀ ፕሮግራም ላይ ነው ተብሏል፡፡
ከገንዘብ ማሰባሰብ ጎን ለጎን የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ለማስከበር የሚያከናውናቸውን ተግባራት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ድርጅቱ ማረጋገጡን አምባሳደር ፍጹም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ጠቅሰዋል፡፡
ネスティッドポートレット
アセットパブリッシャー
— ページごとの項目数 5