ባለፉት 10 ዓመታት ለታላቁ ህዳሴ ግድብ 14 ነጥብ 98 ቢሊየን ብር ከህዝብ መሰብሰቡ ተገለጸ - መነሻ - am

ネスティッドポートレット

アセットパブリッシャー

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ 金, 17 6 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች 水, 8 6 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ 水, 8 6 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

アセットパブリッシャー

ባለፉት 10 ዓመታት ለታላቁ ህዳሴ ግድብ 14 ነጥብ 98 ቢሊየን ብር ከህዝብ መሰብሰቡ ተገለጸ
ባለፉት 10 ዓመታት ለታላቁ ህዳሴ ግድብ 14 ነጥብ 98 ቢሊየን ብር ከህዝብ መሰብሰቡ ተገለጸ
ባለፉት 10 ዓመታት ለታላቁ ህዳሴ ግድብ 14 ነጥብ 98 ቢሊየን ብር ከህዝብ መሰብሰቡን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት አስታወቀ።
ታላቁ ህዳሴ ግድብ የተጀመረበትን 10ኛ ዓመት አስመልክቶ ከመጋቢት 15 እስከ 25 ቀን 2013 ዓ.ም ለ10 ተከታታይ ቀናት የቦንድ ሳምንት እንደሚካሄድ የፅህፈት ቤቱ የህዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ኃይሉ አብርሃም ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የግድቡ የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠበትን ዕለት በማስመልከት በየዓመቱ በመላው ሃገሪቱ የቦንድ ሽያጭ ሳምንት እንደሚያዘጋጁ ኃላፊው አስታውሰዋል።
ከገንዘብ ድጋፉ በተጨማሪ በሀገር ውስጥ እና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለግድቡ አምባሳደር በመሆን አገሪቱ በፍትሃዊ የጋራ ተጠቃሚነት መርህ ግድቡን እየገነባች መሆኗን ዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ እንዲገነዘብ እንዲሁም የሶስተኛ ወገን ጣልቃ-ገብነት እና አድሎአዊ ውሳኔ እንዲቀለበስ ሰፊ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ስራ ሰርተዋል ሲሉ ዳይሬከተሩ ተናግረዋል።
“በዚህም የሀገራችንን ገጽታ ከመገንባት በተጨማሪ በተፈጥሮ ሃብታችን የመጠቀም ሉዓላዊ መብታችንን በማረጋገጥ 10 ዓመታትን በአንድነት በድል የታጀበ ጉዞ አድርገን ግድቡንም 79 በመቶ በማድረስ በማገባደድ ላይ እንገኛለን” ማለታቸውን ኢብኮ ዘግቧል።

ネスティッドポートレット

アセットパブリッシャー

— ページごとの項目数 5
該当件数: 16 件中 1 - 5