ኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል ለሆነችው ኒጀር ገለፃ አደረገች - መነሻ - am

ネスティッドポートレット

アセットパブリッシャー

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ 金, 17 6 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች 水, 8 6 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ 水, 8 6 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

アセットパブリッシャー

ኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል ለሆነችው ኒጀር ገለፃ አደረገች

ኢትዮጵያ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል ለሆነችው ኒጀር ማብራሪያ ሰጠች።

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከኒጀሩ አቻቸው ሞሀመድ ባዞም ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

መሪዎቹ ባደረጉት ውይይት የውሀ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ ኢትዮጵያ የያዘችውን እውነት አስረድተዋል።

ኒጀር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት የወቅቱ ተለዋጭ አባል ሀገራት መካከል አንዷ ናት።

የፀጥታው ምክር ቤት ከኢትዮጵያ ጋር በተገናኘ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን እና በትግራይ ክልል የተደረገውን የሕግ ማስከበር ዘመቻ በተመለከተ አሳስበውኛል የሚላቸውን ጉዳዮች ሲያነሳ እንደነበር ይታወቃል።

የፕሬዝዳንቷ የኒጀር ቆይታም ኒጀር ኢትዮጵያን በተመለከተ በፀጥታው ምክር ቤት በሚነሱ ጉዳዮች ላይ የተሻለ ግንዛቤ እንድትይዝ አድርጓታል ተብሏል።

በቅርቡ የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዶ/ር መሪየም አልሳዲቅ አልመህዲ ግድቡን በተመለከተ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ጋር መወያየታቸው ይታወሳል።

በተመሳሳይ ከዚህ ቀደም የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚንሰትር ሳሚ ሹክሪ የግድቡን ድርድር በተመለከተ የአገራቸውን አቋም ለማንጸባረቅ ወደ ተለያዩ የአፍሪካ አገራት ጉዞ አድርገው ነበር።

ኢትዮጵያም በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የያዘችውን እውነት እና አቋም ለማንፀባረቅ የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ ቀጥላለች።(EBC)

ネスティッドポートレット

アセットパブリッシャー

— ページごとの項目数 5
該当件数: 16 件中 1 - 5