ግብጽ የግድቡ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት የሚፈጥርባት ጫና እንደሌለ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ገለጹ - መነሻ - am

ネスティッドポートレット

アセットパブリッシャー

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ 金, 17 6 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች 水, 8 6 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ 水, 8 6 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

アセットパブリッシャー

ግብጽ የግድቡ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት የሚፈጥርባት ጫና እንደሌለ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ገለጹ

ታላቁ የኢትዮጵያ ግዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በግብጽ ላይ የሚፈጥረው ጫና እንደሌለ ካለም ያንን ለመቋቋመ የሚያስችል በቂ ውሃ እንዳላት የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሽኩሪ ለአገሪቷ ፓርላማ አባላት ገለጸ።
ሑለተኛው ዙር የግድቡ ውሀ ሙሌት በግብጽ ላይ የሚያመጣው ጉዳት እንደሌለ ካለም ለመከላከል መንግስታቸው በቂ ዝግጅት ማድረጉን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ በአስዋን ግድብ በቂ ውሃ መያዛቸውን አብራርተዋል።
"የተደረጉ የቴክኒክ ጥናቶችን ተንተርሼ ነው" ገለጻውን የምሰጣችሁ ያሉት ሚኒስትሩ፤ በዘንድሮው የክረምት ወራት ከፍተኛ ጎርፍ ይጠበቃል፤ ስለሆነም ኢትዮጵያ ግድቧን ውሃ ብትሞላም የሚፈጠር ጫና የለም ከተፈጠረም ጎርፉ ግድባችንን መልሰን ለመሙላት ያግዘናል ብለዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግብጽ ላይ ጉዳት አያስከትልም። ነገር ግን ጉዳት የሚያመጣ ከሆነ በዚህ ረገድ እንደ አገር ያንን ለመቋቋም የሚያስችል በሁሉም መስክ አስፈላጊ ሀብት አለን ሲሉም ነው ሚኒስትሩ የገለጹት።
ኢትዮጵየ የግድቡ መገንባት በግብጽ ላይ የሚፈጥረው ጫና እንደሌለ በተደጋጋሚ ስትገልጽ ቆይታለች፤ የግድቡ ውሃ አሞላልም የታችኛውን የተፋሰሱ አገራት በማይጎዳ መልኩ እንደምታከናውን መግለጿ አይዘነጋም።
(ኢ ፕ ድ)

ネスティッドポートレット

アセットパブリッシャー

— ページごとの項目数 5
該当件数: 16 件中 1 - 5